ዘፀአት 6:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ግባ፥ የግብጽን ንጉሥ ፈርዖንን የእስራኤልን ልጆች ከምድሩ እንዲለቅ ንገረው።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ሂድና ለግብጽ ንጉሥ ለፈርዖን እስራኤላውያን ከአገሩ እንዲወጡ ይፈቅድላቸው ዘንድ ንገረው።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ወደ ግብጽ ንጉሥ ሄደህ እስራኤላውያንን ከአገርህ እንዲወጡ ልቀቃቸው ብለህ ንገረው።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ግባ፤ የእስራኤልን ልጆች ከሀገሩ ይለቅቅ ዘንድ ለግብፅ ንጉሥ ለፈርዖን ንገረው።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) “ግባ፤ የእስራኤልንም ልጆች ከአገሩ ይለቅቅ ዘንድ ለግብፅ ንጉሥ ለፈርዖን ንገር”። |
ከዚህም በኋላ ሙሴና አሮን ሄደው ፈርዖንን እንዲህ አሉት፦ “የእስራኤል አምላክ ጌታ እንዲህ ይላል፦ ‘በምድረ በዳ በዓል እንዲያደርግልኝ ሕዝቤን ልቀቅ።’”