ጌታ ሙሴን እንዳዘዘው ቀንዲሎቹን በጌታ ፊት አበራ።
እግዚአብሔር እንዳዘዘውም መብራቶቹን በእግዚአብሔር ፊት አበራ።
እንዲሁም እግዚአብሔር ባዘዘው መሠረት በዚያ በእግዚአብሔር ፊት መብራቶቹን አበራ።
ቀንዲሎቹንም በእግዚአብሔር ፊት አበራ።
ቀንዲሎቹን በእግዚአብሔር ፊት ለኰሰ።
ሰባቱንም መብራቶች ሥራ፤ በፊት ለፊት እንዲያበሩ መብራቶቹን ከፍ አድርገህ አስቀምጣቸው።
መቅረዙን በመገናኛው ድንኳን ውስጥ፥ በገበታው ፊት ለፊት፥ በማደሪያው በደቡብ በኩል አኖረ፤
ገበታውን ታስገባለህ፥ በአግባቡ ታሰናዳለህ፤ መቅረዙንም አስገብተህ ቀንዲሎቹን ትለኩሳለህ።
“ለአሮን ንገረው እንዲህም በለው መብራቶቹን ስትለኩስ ሰባቱ መብራቶች በመቅረዙ ፊት ያበራሉ።”
አሮንም እንዲሁ አደረገ፤ ጌታ ሙሴን እንዳዘዘው በመቅረዙ ፊት መብራቶቹን ለኰሰ።
ከዙፋኑም መብረቅና ድምፅ ነጐድጓድም ይወጣል፤ በዙፋኑም ፊት ሰባት ችቦዎች ይቀጣጠሉ ነበር፤ እነርሱም ሰባቱ የእግዚአብሔር መናፍስት ናቸው።