Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘፀአት 25:37 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

37 ሰባቱንም መብራቶች ሥራ፤ በፊት ለፊት እንዲያበሩ መብራቶቹን ከፍ አድርገህ አስቀምጣቸው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

37 “ከዚያም ሰባት መብራቶች ሠርተህ ከመቅረዙ ፊት ለፊት ለሚገኘው ስፍራ ብርሃን እንዲሰጡ ከመቅረዙ ላይ አስቀምጣቸው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

37 ለመቅረዙም ሰባት መብራቶች ሠርተህ ከፊት ለፊት በኩል እንዲያበሩ፥ ከፍ አድርገህ አስቀምጣቸው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

37 ሰባ​ቱ​ንም መብ​ራ​ቶች ሥራ፤ በፊቱ ያበሩ ዘንድ መብ​ራ​ቶ​ቹን ያቀ​ጣ​ጥ​ሉ​አ​ቸ​ዋል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

37 ሰባቱንም መብራቶች ሥራ፤ በፊቱ ያበሩ ዝንድ መብራቶቹን ያቀጣጥሉአቸዋል።

Ver Capítulo Copiar




ዘፀአት 25:37
28 Referencias Cruzadas  

በየጥዋቱና በየማታውም ለጌታ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና መዓዛው ያማረ ዕጣን ያሳርጋሉ፤ የተቀደሰውንም ኅብስት በንጹሕ ገበታ ላይ፥ የወርቁን መቅረዝና ቀንዲሎቹንም ማታ ማታ እንዲያበሩ ያዘጋጃሉ፤ እኛም የአምላካችንን የጌታን ትእዛዝ እንጠብቃለን፥ እናንተ ግን ትታችሁታል።


እንዲሁም በቅድስተ ቅዱሳንም ፊት እንደ ሥርዓታቸው እንዲያበሩ መቅረዞችንና ቀንዲሎቻቸውን ከንጹሕ ወርቅ አበጀ።


ሕግህ ለእግሬ መብራት፥ ለመንገዴ ብርሃን ነው።


መኮስተሪያዎችዋንና የኩስታሪ ማስቀመጫዎችዋን ከንጹሕ ወርቅ ሥራ።


ከመጋረጃው ውጭ ባለው በመገናኛው ድንኳን ውስጥ በምስክሩ ታቦት ፊት አሮንና ልጆቹ ከማታ እስከ ማለዳ ድረስ በጌታ ፊት ያሰናዱት፤ በእስራኤል ልጆች ዘንድ በትውልዳቸው የዘለዓለም ሥርዓት ይሁን።”


አሮን በማታ ጊዜ መብራቶቹን ሲያበራ ይጠነው፥ ይህንም በትውልዳችሁ ሁሉ በጌታ ፊት ዘወትር የሚቀርብ ዕጣን ነው።


ሰባቱን መብራቶቹን፥ መኰስተሪያዎቹንና የኩስታሪ ማድረጊያዎቹን ከንጹሕ ወርቅ ሠራ።


መቅረዙን በመገናኛው ድንኳን ውስጥ፥ በገበታው ፊት ለፊት፥ በማደሪያው በደቡብ በኩል አኖረ፤


ጌታ ሙሴን እንዳዘዘው ቀንዲሎቹን በጌታ ፊት አበራ።


ትእዛዝ መብራት፥ ትምህርትም ብርሃን ነውና፥ የተግሣጽም ዘለፋ የሕይወት መንገድ ነውና፥


ወደ ሕጉና ወደ ምስክር ቃሉ ሂዱ! እነርሱም እንዲህ ያለውን ቃል ባይናገሩ የንጋት ብርሃን አይበራላቸውም።


እርሱም፦ “የምታየው ምንድነው?” አለኝ። እኔም፦ “እነሆ፥ ሁለንተናው ወርቅ የሆነ መቅረዝ ይታየኛል፤ የዘይት ማሰሮም በላዩ ላይ ነበረ። በመቅረዙም ላይ ሰባት ቧንቧዎች ያሏቸው ሰባት መብራቶች ነበሩ።


ሰማያዊውንም መጐናጸፊያ ይውሰዱ፥ የመብራቱንም መቅረዝ፥ ቀንዲሎቹንም፥ መቆንጠጫዎቹንም፥ መተርኮሻዎቹንም፥ ዘይቱንም የሚያቀርቡባቸውን ዕቃዎች ሁሉ ይሸፍኑ፤


“ለአሮን ንገረው እንዲህም በለው መብራቶቹን ስትለኩስ ሰባቱ መብራቶች በመቅረዙ ፊት ያበራሉ።”


እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ። በተራራ ላይ ያለች ከተማ ልትደበቅ አትችልም።


እርሱም በጨለማና በሞት ጥላ ተቀምጠው ላሉት ያበራል፤ እግሮቻችንንም ወደ ሰላም መንገድ ይመራል።”


ለሰው ሁሉ የሚያበራው እውነተኛው ብርሃን ወደ ዓለም እየመጣ ነበር።


“ይህ ሽቶ ለሦስት መቶ ዲናር ተሽጦ ለድሆች ለምን አልተሰጠም?” አለ።


ደግሞም ኢየሱስ “እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ፤ የሚከተለኝ የሕይወት ብርሃን ይሆንለታል እንጂ በጨለማ አይመላለስም” ብሎ ተናገራቸው።


የሚናገረኝንም ድምፅ ለማየት ዘወር አልሁ፤ ዘወርም ብዬ ሰባት የወርቅ መቅረዞችን አየሁ፤


በቀኝ እጄ ያየሃቸው የሰባቱ ከዋክብትና የሰባቱ የወርቅ መቅረዞች ምሥጢር ይህ ነው፤ ሰባቱ ከዋክብት የሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት መላእክት ናቸው፤ ሰባቱም መቅረዞች ሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት ናቸው።”


ከዮሐንስ በእስያ ላሉት ለሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት፤ ካለውና ከነበረው፥ ከሚመጣውም፥ በዙፋኑም ፊት ካሉት ከሰባቱ መናፍስት ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን።


ከእንግዲህም ወዲህ ሌሊት አይሆንም፤ ጌታ አምላክም በእነርሱ ላይ ያበራላቸዋልና የመብራት ብርሃንና የፀሐይ ብርሃን አያስፈልጋቸውም፤ ከዘለዓለምም እስከ ዘለዓለም ይነግሣሉ።


ከዙፋኑም መብረቅና ድምፅ ነጐድጓድም ይወጣል፤ በዙፋኑም ፊት ሰባት ችቦዎች ይቀጣጠሉ ነበር፤ እነርሱም ሰባቱ የእግዚአብሔር መናፍስት ናቸው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos