ሑራም ለእያንዳንዱ የዕቃ ማስቀመጫ ዐሥር መታጠቢያ ገንዳዎችን ሠራ፤ እያንዳንዱም ገንዳ ዙሪያ አጋማሽ ስፋት አንድ ሜትር ከሰማንያ ሳንቲ ሜትር ያኽል ሲሆን፥ ስምንት መቶ ሊትር ያኽል ውሃ ይይዝ ነበር።
ዘፀአት 40:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የመታጠቢያውን ሳሕንና ማስቀመጫውን ትቀባዋለህ፥ ትቀድሰዋለህም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የመታጠቢያው ሰንና ማስቀመጫውን ቅባ፤ ቀድሳቸውም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የመታጠቢያውንም ሳሕን ከነማስቀመጫው በዚሁ ዐይነት ቀብተህ ለእግዚአብሔር የተለየ አድርግ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የመታጠቢያውን ሰንና መቀመጫውንም ቀብተህ ትቀድሳለህ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የመታጠቢያውን ሰንና መቀመጫውን ቀብተህ ትቀድሳለህ። |
ሑራም ለእያንዳንዱ የዕቃ ማስቀመጫ ዐሥር መታጠቢያ ገንዳዎችን ሠራ፤ እያንዳንዱም ገንዳ ዙሪያ አጋማሽ ስፋት አንድ ሜትር ከሰማንያ ሳንቲ ሜትር ያኽል ሲሆን፥ ስምንት መቶ ሊትር ያኽል ውሃ ይይዝ ነበር።
እንዲህም ሆነ፤ ሙሴ ማደሪያውን ተክሎ ከጨረሰ በኋላ፥ እርሱንና ዕቃውን ሁሉ ከቀባና ከቀደሰ በኋላ፥ መሠዊያውንና ዕቃውንም ሁሉ ከቀባና ከቀደሰ በኋላ፤