ዘፀአት 39:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲጋጠም በሁለቱ ትከሻዎች ላይ መጋጠሚያ ሠሩለት፥ በሁለቱ ጫፎች እንዲጋጠም አደረጉት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለኤፉዱ ከሁለቱ ጐኖቹ ጋራ ተያይዘው ያሉትን የትከሻ ንጣዮችን ሠሩ፤ ይኸውም ማያያዝ እንዲቻል ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለኤፉዱም ማንገቻ በትከሻ ላይ የሚወርዱ ሁለት ጥብጣቦች ሠርተው ኤፉዱ እንዲጠብቅ በጐንና በጐኑ አያያዙአቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሁለቱ ወገን እንዲጋጠሙ፥ በሁለት ጫንቃዎች ላይ የሚጋጠም ልብሰ መትከፍ ሠሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሁለቱ ወገን እንዲጋጠም በሁለቱ ጫንቃዎች ላይ የሚጋጠም ልብስ አደረጉት። |
ወርቁንም ቀጥቅጠው እንደ ቅጠል ስስ አድርገው እንደ ፈትል ቆረጡት። ብልህ ሠራተኛ እንደሚሠራው በሰማያዊው፥ በሐምራዊው፥ በቀዩ ግምጃ፥ በተፈተለው ጥሩ በፍታ መካከል በእርሱ ጠለፉ።
በላዩም መታጠቂያ ሆኖ በብልሃት የተጠለፈው የኤፉዱ ቋድ እንደ እርሱ ከወርቅ፥ ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊ፥ ከቀይ ግምጃና ከተፈተለ ጥሩ በፍታ የተሠራ ነበረ፥ ጌታ ሙሴን እንዳዘዘው ከእርሱ ጋር ወጥ ሆኖ የተሠራ ነበር።