ዘፀአት 39:30 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የተቀደሰውን አክሊል አበባ ከንጹሕ ወርቅ ሠሩ፤ በእርሱም እንደ ማኅተም “ለጌታ የተቀደሰ” የሚል ጽሑፍ ቀረጹበት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከንጹሕ ወርቅ የተቀደሰውን አክሊል ሰሌዳ ሠርተው፣ በማኅተም ላይ እንደ ተቀረጸ ጽሑፍ፤ ቅዱስ ለእግዚአብሔር የሚል ቀረጹበት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የተቀደሰውንም የአክሊል ምልክት ከንጹሕ ወርቅ ሠርተው “ለእግዚአብሔር አገልግሎት የተለየ” የሚል ቃል እንደ ማኅተም ቀረጹበት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከጥሩ ወርቅ የተለየ የወርቅ ቅጠል ሠሩ፤ በእርሱም እንደ ማኅተም ቅርጽ አድርገው፥ “ቅድስና ለእግዚአብሔር” የሚል ጻፉበት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም ሙሴን እንዳዘዘው፥ ከጥሩ ወርቅ የተቀደሰውን የአክሊል ምልክት ሠሩ፤ በእርሱም እንደ ማኅተም ቅርጽ አድርገው፦ ቅድስና ለእግዚአብሔር የሚል ጻፉበት። |
መድኃኒታችንም ከኃጢአት ሁሉ እንዲቤዠን፥ መልካሙንም ለማድረግ የሚቀናውን ገንዘቡም የሚሆነውን ሕዝብ ለራሱ እንዲያነጻ፥ ስለ እኛ ነፍሱን ሰጥቶአል።