Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘፀአት 39:30 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

30 የተቀደሰውንም የአክሊል ምልክት ከንጹሕ ወርቅ ሠርተው “ለእግዚአብሔር አገልግሎት የተለየ” የሚል ቃል እንደ ማኅተም ቀረጹበት።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

30 ከንጹሕ ወርቅ የተቀደሰውን አክሊል ሰሌዳ ሠርተው፣ በማኅተም ላይ እንደ ተቀረጸ ጽሑፍ፤ ቅዱስ ለእግዚአብሔር የሚል ቀረጹበት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

30 የተቀደሰውን አክሊል አበባ ከንጹሕ ወርቅ ሠሩ፤ በእርሱም እንደ ማኅተም “ለጌታ የተቀደሰ” የሚል ጽሑፍ ቀረጹበት።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

30 ከጥሩ ወርቅ የተ​ለየ የወ​ርቅ ቅጠል ሠሩ፤ በእ​ር​ሱም እንደ ማኅ​ተም ቅርጽ አድ​ር​ገው፥ “ቅድ​ስና ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር” የሚል ጻፉ​በት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

30 እግዚአብሔርም ሙሴን እንዳዘዘው፥ ከጥሩ ወርቅ የተቀደሰውን የአክሊል ምልክት ሠሩ፤ በእርሱም እንደ ማኅተም ቅርጽ አድርገው፦ ቅድስና ለእግዚአብሔር የሚል ጻፉበት።

Ver Capítulo Copiar




ዘፀአት 39:30
11 Referencias Cruzadas  

“ለድንኳኑም ደጃፍ ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊና ከቀይ ከፈይ ከተፈተለ ከጥሩ በፍታ በጥልፍ ያጌጠ መጋረጃ አድርግለት።


መታጠቂያውንም ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊና ከቀይ ከፈይ ከተፈተለ ጥሩ በፍታ ሠርተው እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት በጥልፍ ጥበብ አስጌጡት።


እርሱንም እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት ከመጠምጠሚያው ፊት በሰማያዊ ክር አሰሩት።


በዚያን ጊዜ በፈረሶች አንገት ላይ በሚንጠለጠል ቃጭል ሁሉ ላይ “ለእግዚአብሔር የተለየ” የሚል የጽሕፈት ምልክት ይቀረጽበታል፤ በቤተ መቅደሱ ውስጥ ያለው የማብሰያ ማሰሮ በመሠዊያው ላይ እንደሚገኘው ሳሕን የተቀደሰ ይሆናል።


እናንተን ግን እግዚአብሔር ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ኅብረት እንዲኖራችሁ አደረገ፤ ስለዚህ እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስን ጥበባችን፥ ጽድቃችን፥ ቅድስናችንና ቤዛችን እንዲሆን አደረገው።


እኛ በክርስቶስ የእግዚአብሔር ጽድቅ ተካፋዮች እንድንሆን እግዚአብሔር ኃጢአት የሌለበትን ክርስቶስን የእኛን ኃጢአት እንዲሸከም አደረገው።


ክርስቶስ ከዐመፃ ሁሉ ሊያድነንና መልካም ሥራ ለመሥራት ትጉሆችና ለእርሱ የተለየን ንጹሕ ሕዝብ እንድንሆን ያነጻን ዘንድ ስለ እኛ ራሱን አሳልፎ ሰጠ።


እርሱ የእግዚአብሔር ክብር ነጸብራቅ ነው፤ እርሱ በባሕርዩ ከእግዚአብሔር ጋር ፍጹም ትክክል ነው። በኀያል ቃሉ ዓለምን ሁሉ ደግፎ ይዞአል፤ ሰዎችንም ከኃጢአት ካነጻ በኋላ በሰማይ በኀያሉ እግዚአብሔር ቀኝ ተቀምጦአል።


እንዲህ ያለው ቅዱስ፥ ነቀፋ የሌለበት፥ ንጹሕ፥ ከኃጢአተኞች የተለየ፥ ከሰማይ በላይ ከፍ ያለ የካህናት አለቃ ያስፈልገናል።


ለአምላካችንም የካህናት መንግሥት እንዲሆኑ አድርገሃቸዋል፤ በምድርም ላይ ይነግሣሉ።”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos