ዘፀአት 39:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሁለቱንም የተጐነጐኑትን የወርቅ ድሪዎች በደረቱ ኪስ ጫፎች ባሉት በሁለቱ ቀለበቶች አስገቡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሁለቱን የወርቅ ድሪዎች በደረት ኪሱ ጐንና ጐን ካሉት ቀለበቶች ጋራ አያያዟቸው፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሁለቱንም የወርቅ ድሪዎች ከቀለበቶቹ ጋር እንዲያያዙ አደረጉ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሁለቱንም የተጐነጐኑትን የወርቅ ድሪዎች በልብሰ እንግድዓው በሁለቱ ወገኖች ወዳሉት ወደ ሁለቱ ቀለበቶች አገቡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሁለቱንም የተጐነጐኑትን የወርቅ ድሪዎች በደረቱ ኪስ ወገኖች ወዳሉት ወደ ሁለቱ ቀለበቶች አገቡ። |