ዘፀአት 39:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለደረቱ ኪስም እንደ ገመድ የተጐነጐኑ ድሪዎችን ከንጹሕ ወርቅ ሠሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለደረት ኪሱም ልክ እንደ ገመድ ከንጹሕ ወርቅ የተጐነጐኑ ድሪዎችን አበጁለት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለደረቱ ኪስም እንደ ገመድ የተጐነጐኑትን ድሪዎች ከጥሩ ወርቅ ሠሩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለልብሰ እንግድዓውም የተጐነጐኑትን ድሪዎች እንደ ገመድ አድርገው ከጥሩ ወርቅ ሠሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለደረቱ ኪስም የተጐነጐኑትን ድሪዎች እንደ ገመድ አድርገው ከጥሩ ወርቅ ሠሩ። |
የዕንቁዎቹም ድንጋዮች እንደ ዐሥራ ሁለቱ እንደ እስራኤል ልጆች ስሞች ነበሩ፥ በየስማቸውም ማተሚያ እንደሚቀረጽ ተቀረጹ፥ ስለ ዐሥራ ሁለቱም ነገዶች ነበሩ።
ከእነርሱ ጋር በዓለም ሳለሁ የሰጠኸኝን እኔ በስምህ እጠብቃቸው ነበር፤ ጠበቅኋቸውም፤ የመጽሐፉም ቃል እንዲፈጸም ከጥፋት ልጅ በቀር ከእነርሱ ማንም አልጠፋም።