በአንደኛው ቅርንጫፍ እንቡጥና ቀንበጥ ያለው የለውዝ አበባ የሚመስሉ ሦስት ጽዋዎች፥ በሁለተኛውም ቅርንጫፍ እንቡጥና ቀንበጥ ያለው የለውዝ አበባ የሚመስሉ ሦስት ጽዋዎች አድርግ፤ እንዲሁም ከመቅረዙ ለሚወጡ ለስድስቱ ቅርንጫፎች አድርግ።
ዘፀአት 37:21 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከመቅረዙ ለወጡ ለስድስት ቅርንጫፎች ከሁለት ቅርንጫፎች በታች አንድ ሆኖ የተሠራ አንድ ጉብጉብ፥ ከሁለትም ቅርንጫፎች በታች አንድ ሆኖ የተሠራ አንድ ጉብጉብ፥ ደግሞ ከሁለት ቅርንጫፎች በታች አንድ ሆኖ የተሠራ አንድ ጉብጉብ ነበረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንደኛው እንቡጥ ከመቅረዙ ወጣ ብለው በሚገኙት በመጀመሪያው ጥንድ ቅርንጫፎች ሥር፣ ሁለተኛውም እምቡጥ በሁለተኛው ጥንድ ሥር እንዲሁም ሦስተኛው እንቡጥ በሦስተኛው ጥንድ ሥር ነበር፤ በስድስቱም ቅርንጫፎች እንዲሁ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከሦስቱም ጥንድ ቅርንጫፎች በእያንዳንዱ ጥንድ ሥር አንድ እንቡጥ ተስሎ ነበር፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከመቅረዝዋ ለወጡ ለስድስት ቅርንጫፎች ከሁለት ቅርንጫፎች በታች አንድ ሆኖ የተሠራ አንድ ጕብጕብ፥ ከሁለትም ቅርንጫፎች በታች አንድ ሆኖ የተሠራ አንድ ጕብጕብ፥ ደግሞ ከሁለት ቅርንጫፎች በታች አንድ ሆኖ የተሠራ አንድ ጕብጕብ ነበረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከመቅረዙ ለወጡ ለስድስት ቅርንጫፎች ከሁለት ቅርንጫፎች በታች አንድ ሆኖ የተሠራ አንድ ጕብጕብ፥ ከሁለትም ቅርንጫፎች በታች አንድ ሆኖ የተሠራ አንድ ጕብጕብ፥ ደግሞ ከሁለት ቅርንጫፎች በታች አንድ ሆኖ የተሠራ አንድ ጕብጕብ ነበረ። |
በአንደኛው ቅርንጫፍ እንቡጥና ቀንበጥ ያለው የለውዝ አበባ የሚመስሉ ሦስት ጽዋዎች፥ በሁለተኛውም ቅርንጫፍ እንቡጥና ቀንበጥ ያለው የለውዝ አበባ የሚመስሉ ሦስት ጽዋዎች አድርግ፤ እንዲሁም ከመቅረዙ ለሚወጡ ለስድስቱ ቅርንጫፎች አድርግ።
ከመቅረዙ ለሚወጡ ለስድስቱ ቅርንጫፎች ከሁለት ቅርንጫፎች በታች አንድ ሆኖ የተሠራ አንድ እንቡጥ፥ ከሁለት ቅርንጫፎች በታች አንድ ሆኖ የተሠራ አንድ እንቡጥ፥ ደግሞ ከሁለት ቅርንጫፎች በታች አንድ ሆኖ የተሠራ አንድ እንቡጥ ይሁን።