“ከንጹሕ ወርቅ መቅረዝ ሥራ፤ መቅረዙ የተቀጠቀጠ ሥራ ይሁን፤ እግሩና ከአገዳው ጋር ጽዋዎቹም ጉብጉቦቹም አበቦቹም አንድነት በእርሱ ይደረጉበት።
ዘፀአት 37:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በመቅረዙም ጉብጉቦቹንና አበቦቹን አራትም የለውዝ አበባ የሚመስሉትን ጽዋዎች አደረገ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንቡጦችና የፈኩ አበቦች ያሉባቸው የለውዝ አበባ የሚመስሉ አራት ጽዋዎች በመቅረዙ ላይ ነበሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የመቅረዙም ዘንግ እንቡጥና ቀንበጥ ያላቸውን የለውዝ አበባዎችን የሚመስሉ አራት የጌጠኛ አበባ ወርዶች ተስለውበት ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በመቅረዝዋም ጕብጕቦችዋንና አበቦችዋን፥ አራትም የለውዝ አበባ የሚመስሉትን ጽዋዎች አደረገ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በመቅረዙም ጕብጕቦቹንና አበቦቹን አራትም የለውዝ አበባ የሚመስሉትን ጽዋዎች አደረገ። |
“ከንጹሕ ወርቅ መቅረዝ ሥራ፤ መቅረዙ የተቀጠቀጠ ሥራ ይሁን፤ እግሩና ከአገዳው ጋር ጽዋዎቹም ጉብጉቦቹም አበቦቹም አንድነት በእርሱ ይደረጉበት።
በአንደኛው ቅርንጫፍ እንቡጥና ቀንበጥ ያለው የለውዝ አበባ የሚመስሉ ሦስት ጽዋዎች፥ በሁለተኛውም ቅርንጫፍ እንቡጥና ቀንበጥ ያለው የለውዝ አበባ የሚመስሉ ሦስት ጽዋዎች አድርግ፤ እንዲሁም ከመቅረዙ ለሚወጡ ለስድስቱ ቅርንጫፎች አድርግ።
በአንደኛው ቅርንጫፍ እንቡጥ፥ ቀንበጥ ያለው የለውዝ አበባ የሚመስሉ ሦስት ጽዋዎች፥ በሁለተኛውም ቅርንጫፍ እንቡጥ፥ ቀንበጥ ያለው የለውዝ አበባ የሚመስሉ ሦስት ጽዋዎች፥ እንዲሁም ከመቅረዙ ለወጡ ለስድስቱ ቅርንጫፎች አደረገ።
ከመቅረዙ ለወጡ ለስድስት ቅርንጫፎች ከሁለት ቅርንጫፎች በታች አንድ ሆኖ የተሠራ አንድ ጉብጉብ፥ ከሁለትም ቅርንጫፎች በታች አንድ ሆኖ የተሠራ አንድ ጉብጉብ፥ ደግሞ ከሁለት ቅርንጫፎች በታች አንድ ሆኖ የተሠራ አንድ ጉብጉብ ነበረ።
ከፍ ያለውን ደግሞ ሲፈሩ፥ ድንጋጤም በመንገድ ላይ ሲሆን፥ ለውዝም ሲያብብ፥ አንበጣም እንደ ሸክም ሲከብድ፥ ፈቃድም ሲጠፋ፥ ሰው ወደ ዘለዓለም ቤት ሲሄድ፥ አልቃሾችም በአደባባይ ሲዞሩ፥
እንዲህም ሆነ፤ በማግስቱ ሙሴ ወደ ምስክሩ ድንኳን ውስጥ ገባ፤ እነሆም፥ ለሌዊ ቤት የሆነው የአሮን በትር አቈጥቁጦ፥ እምቡጥም አውጥቶ፥ አበባም አብቦ፥ የበሰለ ለውዝም አፍርቶ ነበር።