ውስጡንና ውጪውን በንጹሕ ወርቅ ለበጠው፤ በዙሪያውም የወርቅ ክፈፍ አደረገለት።
በውስጥና በውጭ በንጹሕ ወርቅ ለበጠው፤ በዙሪያውም የወርቅ ክፈፍ አበጀለት።
ውስጡንም ውጪውንም በጥሩ ወርቅ ለበጠው፤ በዙሪያውም የወርቅ ክፈፍ አደረገለት፤
በውስጥዋም፥ በውጭዋም በጥሩ ወርቅ ለበጣት፤ በዙሪያዋም የወርቅ አክሊል አደረገላት።
በውስጥም በውጭም በጥሩ ወርቅ ለበጠው፤ በዙሪያውም የወርቅ አክሊል አደረገለት።
ላዩን፥ የጎኖቹን ዙሪያ ሁሉና ቀንዶቹን በንጹሕ ወርቅ ትለብጠዋለህ፤ ዙሪያው የወርቅ አክሊል ታደርግለታለህ።
ባስልኤል ከግራር እንጨት ታቦቱን ሠራ፤ ርዝመቱ ሁለት ክንድ ተኩል፥ ወርዱ አንድ ክንድ ተኩል፥ ቁመቱም አንድ ክንድ ተኩል ነበር።
በአራቱ እግሮቹ ላይ አራት የወርቅ ቀለበቶችን አደረገለት፤ በአንድ በኩል ሁለት ቀለበቶችን፥ በሌላው በኩል ሁለት ቀለበቶች ሆኑ።