ዘፀአት 37:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በጎኑም ስድስት ቅርንጫፎች ወጡለት፤ ሦስቱ የመቅረዙ ቅርንጫፎች በአንድ በኩል፥ ሦስቱም የመቅረዙ ቅርንጫፎች በሌላ በኩል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሦስቱ በአንድ በኩል ሦስቱ በሌላ በኩል በመሆን ስድስት ቅርንጫፎች ከመቅረዙ ጐኖች ተሠርተው ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በአንድ በኩል ሦስት፥ በሌላ በኩል ሦስት በመሆን ከጐኖቹ ስድስት ቅርንጫፎች እንዲወጡ አደረገ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በስተጎንዋ ስድስት ቅርንጫፎች ወጡላት፤ ሦስቱ የመቅረዝዋ ቅርንጫፎች በአንድ ወገን፥ ሦስቱም የመቅረዝዋ ቅርንጫፎች በሁለተኛው ወገን ወጡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በስተጎኑም ስድስት ቅርንጫፎች ወጡለት፤ ሦስቱ የመቅረዙ ቅርንጫፎች በአንድ ወገን፥ ሦስቱም የመቅረዙ ቅርንጫፎች በሌላ ወገን ወጡ። |
መቅረዙን ከንጹሕ ወርቅ ሠራ፤ መቅረዙንም ከእግሩና ከአገዳው ጋር በተቀረጸ ሥራ አደረገ፤ ጽዋዎቹን፥ ጉብጉቦቹን፥ አበቦቹን ከዚያው በአንድነት አደረገ።
በአንደኛው ቅርንጫፍ እንቡጥ፥ ቀንበጥ ያለው የለውዝ አበባ የሚመስሉ ሦስት ጽዋዎች፥ በሁለተኛውም ቅርንጫፍ እንቡጥ፥ ቀንበጥ ያለው የለውዝ አበባ የሚመስሉ ሦስት ጽዋዎች፥ እንዲሁም ከመቅረዙ ለወጡ ለስድስቱ ቅርንጫፎች አደረገ።