ዘፀአት 37:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዙሪያው አንድ ስንዝር የሚያህል ክፈፍ አደረገለት፤ የወርቅ አክሊል በክፈፉ ዙሪያ አደረገለት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዙሪያውም ስፋቱ አንድ ስንዝር የሆነ ጠርዝ በማበጀት በጠርዙ ላይ የወርቅ ክፈፍ አደረጉበት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ደግሞም በዙሪያው ሰባ አምስት ሚሊ ሜትር ስፋት ያለው ጠርዝና በጠርዙም ዙሪያ የወርቅ ክፈፍ አደረገለት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዙሪያውም አንድ ጋት የሚያህል ክፈፍ አደረገለት፤ የወርቅም አክሊል በክፈፉ ዙሪያ አደረገለት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዙሪያውም አንድ ጋት የሚያህል ክፈፍ አደረገለት፤ የወርቅም አክሊል በክፈፉ ዙሪያ አደረገለት። |