ዘፀአት 36:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የመቅደሱን ሥራ የሚሠሩ ጠቢባን ሁሉ ሥራቸውን ትተው መጡ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ የመቅደሱን ሥራ ሁሉ ይሠሩ የነበሩ ጥበበኞች የሆኑ ባለሙያዎች ሁሉ ሥራቸውን ትተው መጡ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህም በኋላ ሥራውን የሚያከናውኑት ጥበበኞች ሁሉ ሥራቸውን ትተው ወደ ሙሴ በመሄድ፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እያንዳንዳቸው በሚሠሩት የመቅደሱን ሥራ የሚሠሩ ጠቢባን ሁሉ መጡ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የመቅደሱንም ሥራ የሚሠሩ ጠቢባን ሁሉ የሚያደርጉትን ሥራ ትተው መጡ፥ |
የመቅደሱን ሥራ ለመሥራት የእስራኤል ልጆች ያመጡትን ስጦታ ሁሉ ከሙሴ ወሰዱ። እነዚያም በፈቃዳቸው የሚያቀርቡትን ስጦታ አሁንም ማለዳ ማለዳ ወደ እርሱ ያመጡ ነበር።
የእግዚአብሔር ጸጋ እንደተሰጠኝ መጠን እንደ ብልኅ ግንበኛ መሠረትን ጣልኩ፤ ሌላውም በዚያ ላይ ያንጻል። እያንዳንዱ ግን በዚያ ላይ እንዴት እንደሚያንጽ ይጠንቀቅ።