ዘፀአት 36:31 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከግራር እንጨት መወርወሪያዎችን ሠራ፥ በማደሪያው በአንደኛው በኩል ላሉት ሳንቃዎች አምስት፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንደዚሁም ከግራር ዕንጨት አግዳሚዎችን ሠሩ፤ በማደሪያው ድንኳን በአንድ በኩል ላሉት ወጋግራዎች ዐምስት አግዳሚዎችን ሠሩ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዐሥራ አምስት መወርወሪያዎችንም ከግራር እንጨት ሠሩ፤ በዚህ ዐይነት አምስቱ ከድንኳኑ በአንድ በኩል ላሉት ተራዳዎች ሲሆኑ፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከማይነቅዝ ዕንጨት በድንኳኑ በአንደኛው ወገን ላሉት ሳንቆች አምስት መወርወሪያዎችን፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከግራርም እንጨት በማደሪያው በአንደኛው ወገን ላሉት ሳንቆች አምስት መወርወሪያዎች፥ |
በማደሪያው በሁለተኛው በኩል ላሉት ሳንቃዎች አምስት መወርወሪያዎች፥ ከማደሪያው በስተ ኋላ በምዕራቡ በኩል ላሉት ሳንቃዎች አምስት መወርወሪያዎችን ሠራ።