እርሱም፦ “እኔ ደግሞ አንድ ጊዜ ብቻ ብናገር ጌታዬ አይቆጣ፥ ምናልባት ከዚያ ዐሥር ቢገኙሳ?” አለ። እርሱም፦ “ስለ አሥሩ አላጠፋትም” አለ።
ዘፀአት 33:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ ሙሴን፦ “በፊቴ ሞገስን ስላገኘህና በስምህም ስላወቅሁህ ይህን ያልኸውን ነገር ሁሉ አደርጋለሁ” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔርም ሙሴን፣ “በአንተ ደስ ስላለኝና በስም ስለማውቅህ፣ የጠየቅኸውን ያንኑ አደርጋለሁ” አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔርም ሙሴን “እኔ አንተን በሚገባ በትክክል ስለማውቅህና በአንተም ደስ ስለምሰኝ የምትለውን ሁሉ አደርጋለሁ” አለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፥ “ይህን ያልኸኝን ነገር አደርግልሃለሁ፤ በፊቴ ሞገስን አግኝተሀልና ከሁሉ ይልቅ ዐውቄሃለሁና”አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም ሙሴን፦ በፊቴ ሞገስ ስላገኘህ በስምህም ስላወቅሁህ ይህን ያልኸውን ነገር አደርጋለሁ አለው። |
እርሱም፦ “እኔ ደግሞ አንድ ጊዜ ብቻ ብናገር ጌታዬ አይቆጣ፥ ምናልባት ከዚያ ዐሥር ቢገኙሳ?” አለ። እርሱም፦ “ስለ አሥሩ አላጠፋትም” አለ።
እነሆ ባርያህ በፊትህ ሞገስን አግኝቶአል፥ ነፍሴን ለማዳን ያደረግህልኝን ምሕረትህንም አብዝተሃል፥ ክፉ እንዳያገኘኝና እንዳልሞት ወደ ተራራ ሸሽቼ አመልጥ ዘንድ አልችልም፥
ሙሴ ጌታን እንዲህ አለው፥ “እይ! አንተ ‘ይህን ሕዝብ አውጣ’ ብለኸኛል፥ ነገር ግን ከእኔ ጋር የምትልከውን አላስታወቅኸኝም። አንተም፦ ‘በስምህ አወቅሁህ፥ ደግሞም በእኔ ፊት ሞገስን አግኝተሃል’ ብለኸኝ ነበር።
በስምህም የምጠራህ የእስራኤል አምላክ ጌታ እኔ እንደሆንሁ ታውቅ ዘንድ በጨለማ የነበረችውን መዝገብ በስውርም የተደበቀችውን ሀብት እሰጥሃለሁ።
ስለዚህ ኀጢአታችሁን እርስ በርሳችሁ ተናዘዙ፤ ትፈወሱም ዘንድ አንዱ ለሌላው ይጸልይ። የጻድቅ ሰው ጸሎት ኃይል አለው፤ ታላቅ ነገርም ያደርጋል።