ግመሎቹም ከጠጡ በኋላ እንዲህ ሆነ፥ ሰውዬው ግማሽ ሰቅል የሚመዝን የወርቅ ቀለበት፥ ለእጆችዋም ዐሥር ሰቅል የሚመዘን ጥንድ የወርቅ አምባር አወጣ፥
ዘፀአት 32:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሮንም፦ “በሚስቶቻችሁ፥ በወንዶችና በሴቶች ልጆቻችሁ ጆሮ ያሉትን የወርቅ ቀለበቶች ሰብራችሁ አምጡልኝ” አላቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አሮንም፣ “የሚስቶቻችሁን፣ የወንድና የሴት ልጆቻችሁን የጆሮ ወርቅ አውልቃችሁ ወደ እኔ አምጡ” ብሎ መለሰላቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አሮንም “ሚስቶቻችሁ፥ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁ የሚያጌጡበትን የጆሮ ወርቅ ሁሉ ሰብስባችሁ አምጡልኝ” አላቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሮንም፥ “በሚስቶቻችሁና በሴቶች ልጆቻችሁ ጆሮ ያሉትን የወርቅ ጌጦች አምጡልኝ” አላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሮንም፦ በሚስቶቻችሁ በወንዶችና በሴቶች ልጆቻችሁም ጆሮ ያሉትን የወርቅ ቀለበቶች ሰብራችሁ አምጡልኝ አላቸው። |
ግመሎቹም ከጠጡ በኋላ እንዲህ ሆነ፥ ሰውዬው ግማሽ ሰቅል የሚመዝን የወርቅ ቀለበት፥ ለእጆችዋም ዐሥር ሰቅል የሚመዘን ጥንድ የወርቅ አምባር አወጣ፥
እኔም፦ ‘አንቺ የማን ልጅ ነሽ?’ ብዬ ጠየቅኋት። እርሷም፦ ‘ሚልካ ለናኮር የወለደችለት የባቱኤል ልጅ ነኝ’ አለች፥ ቀለበትም አደረግሁላት፥ ለእጆችዋም አምባሮች አደረግሁላት።
ልባቸው የተነሣሣ ወንዶችና ሴቶች ሁሉ የአፍንጫ ጌጦችን፥ ሎቲዎችን፥ ቀለበቶችን፥ ድሪዎችን፥ የወርቅ ጌጦችን ሁሉ አመጡ፤ ሰዎች ሁሉ የወርቅ ስጦታ ለጌታ አመጡ።
በብርም የተለበጡትን የተቀረጹትን ምስሎችህን፥ በወርቅም የተለበጡትን ቀልጠው የተሠሩትን ምስሎችህን ታረክሳለህ፤ እንደ ርኩስም ነገር ትጥላቸዋለህ፦ “ከእኔ ራቁ!” ትላቸዋለህ።