ዘፀአት 32:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱም፦ “ይህ የድል ነሺዎች ድምጽ ወይም የድል ተነሺዎች ድምፅ አይደለም፥ ነገር ግን የዘፈን ድምፅ እሰማለሁ” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሙሴም፣ “የድል ድምፅ አይደለም፤ የሽንፈትም ድምፅ አይደለም፤ የምሰማው የዘፈን ድምፅ ነው” ብሎ መለሰለት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሙሴም “ይህ የምሰማው የዘፈን ድምፅ እንጂ የድል አድራጊዎች ድንፋታ ወይም የተሸነፈ ሕዝብ የለቅሶ ጫጫታ አይደለም” አለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሙሴም፥ “ይህ የድል ነሺዎች ወይም የድል ተነሺዎች ድምፅ አይደለም፤ ነገር ግን የወይን ስካር ድምፅ እሰማለሁ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም፦ ይህ የድል ነሺዎች ወይም የድል ተነሺዎች ድምፅ አይደለም፥ ነገር ግን የዘፈን ድምፅ እሰማለሁ አለው። |