በቆጠራው የሚያልፉ ሁሉ ይህን ይስጡ፥ በመቅደሱ ሰቅል ሚዛን መሠረት ግማሽ ሰቅል ይሰጣል፥ ሰቅል ሃያ ጌራ ነው፤ ግማሽ ሰቅል ለጌታ ስጦታ ነው።
ዘፀአት 30:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚህ ቆጠራ የሚያልፍ፥ ሃያ ዓመት የሞላውና ከዚያም በላይ የሆነ ሁሉ፥ ይህንን ስጦታ ለጌታ ይስጥ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዕድሜያቸው ሃያ ዓመትና ከሃያ በላይ ሆኖ ወደ ተቈጠሩት ያለፉት ሁሉ፣ ለእግዚአብሔር መሥዋዕት ማቅረብ አለባቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከሕዝብ ቈጠራው ለመግባት ዕድሜው የፈቀደለት፥ ማለትም ኻያ ዓመት የሞላውና ከዚያም በላይ የሆነ ሁሉ ይህን የእግዚአብሔር መባ ያቅርብ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይቈጠር ዘንድ የሚያልፈው ሁሉ፥ ከሃያ ዓመት ጀምሮ ከዚያም ከፍ ያለ፥ የእግዚአብሔርን ስጦታ ይሰጣል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰቅሉ ሀያ ኦቦሊ ነው። አልፎ የተቆጠረ ሁሉ፥ ከሀያ አመት ጀምሮ ከዚያም ከፍ ያለ፥ የእግዚአብሔርን ስጦታ ይሰጣል። |
በቆጠራው የሚያልፉ ሁሉ ይህን ይስጡ፥ በመቅደሱ ሰቅል ሚዛን መሠረት ግማሽ ሰቅል ይሰጣል፥ ሰቅል ሃያ ጌራ ነው፤ ግማሽ ሰቅል ለጌታ ስጦታ ነው።
በሁለተኛውም ወር በመጀመሪያው ቀን ማኅበሩን ሁሉ ሰብሰቡአቸው፤ እነርሱም ዕድሜው ሀያ ዓመት የሆነውንና ከዚያም በላይ ያለውን አንድ በአንድ እንደየስማቸው ቍጥር፥ በየወገኖቻቸው በየአባቶቻቸውም ቤቶች ትውልዳቸውን መዘገቡ።
“የእስራኤል በኩር የሮቤል ልጆች በየትውልዳቸው፥ በየወገኖቻቸው፥ በየአባቶቻቸው ቤቶች፥ እንደየስማቸው ቍጥር፥ አንድ በአንድ፥ ዕድሜው ሀያ ዓመት የሆነውንና ከዚያም በላይ ያለውን ወንድ ሁሉ፥ ወደ ጦርነት የሚወጣው ሁሉ፥
በድኖቻችሁ በዚህ ምድረ በዳ ይወድቃሉ፤ ከአጠቃላይም ቁጥራችሁ፥ በእኔ ላይ ያጉረመረሙ ዕድሜአቸው ሀያ ዓመት የሆናቸውና ከዚያም በላይ ሆነው የተቈጠሩት ሁሉ፥
“ዕድሜው ሀያ ዓመት የሆነውንና ከዚያም በላይ ያለውን፥ በእስራኤል ወደ ጦርነት የሚወጣውን ሁሉ፥ የእስራኤልን ልጆች ማኅበር ሁሉ በየአባቶቻቸው ቤት ቁጠሩ።”
‘ከግብጽ የወጡት ዕድሜአቸው ሀያ ዓመት የሞላቸውና ከዚያም በላይ ያሉት ሰዎች እኔን ፈጽመው አልተከተሉምና ለአብርሃምና ለይስሐቅ ለያዕቆብም ለመስጠት የማልሁላቸውን ምድር አያዩም፤