La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘፀአት 3:22 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ነገር ግን እያንዳንዲቱ ሴት ከጎረቤትዋ በቤትዋም ካለችው ሴት የብር እቃ የወርቅ እቃ ልብስም ትለምናለች፤ በወንዶችና በሴቶች ልጆቻችሁ ላይ ታደርጉታላችሁ፤ ግብፃውያንንም ትበዘብዛላችሁ።”

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እያንዳንዷ ዕብራዊት ከጎረቤቷም ይሁን ዐብራት ከምትኖረው ግብጻዊት የብርና የወርቅ ጌጣጌጦች እንደዚሁም ልብስ እንድትሰጣት ትጠይቅ። እነዚህንም ሁሉ ወስዳችሁ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁን ታስጌጧቸዋላችሁ፤ ታለብሷቸዋላችሁም። በዚህም መንገድ የግብጻውያኑን ሀብት በእጃችሁ አግብታችሁ ትወጣላችሁ።”

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

የዕብራውያን ሴቶች እያንዳንዳቸው ጐረቤት በመሆን አብረዋቸው የሚኖሩትን ግብጻውያን ሴቶች ወርቅ፥ ብርና፥ ጌጣጌጥና ልብስ እንዲሰጡአቸው ይጠይቃሉ፤ ይህንንም ሁሉ ወስዳችሁ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁን ታለብሳላችሁ፤ በዚህም ዐይነት ግብጻውያንን በዝብዛችሁ ትወጣላችሁ።”

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ነገር ግን እያ​ን​ዳ​ን​ዲቱ ሴት ከጎ​ረ​ቤቷ፥ በቤ​ቷም ካለ​ችው ሴት የብር ዕቃ፥ የወ​ርቅ ዕቃ፥ ልብ​ስም ትዋ​ሳ​ለች፤ በወ​ን​ዶ​ችና በሴ​ቶች ልጆ​ቻ​ችሁ ላይም ታደ​ር​ጉ​ታ​ላ​ችሁ፤ ግብ​ፃ​ው​ያ​ን​ንም ትበ​ዘ​ብ​ዛ​ላ​ችሁ።”

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ነገር ግን እያንዳንዲቱ ሴት ከጎረቤትዋ በቤትዋም ካለችው ሴት የብር ዕቃ የወርቅ እቃ ልብስም ትለምናለች፤ በወንዶችና በሴቶች ልጆቻችሁ ላይ ታደርጉታላችሁ፤ ግብፃውያንንም ትበዘብዛላችሁ።”

Ver Capítulo



ዘፀአት 3:22
9 Referencias Cruzadas  

ደግሞም በባርነት በሚገዙአቸው ሕዝብ ላይ እኔ እፈርዳለሁ፥ ከዚያም በኋላ በብዙ ከብት ይወጣሉ።


ሎሌውም የብርና የወርቅ ጌጥ ልብስም አወጣ፥ ለርብቃም ሰጣት፥ የከበረ ስጦታንም ለወንድምዋና ለእናትዋ አቀረበ።


ከወርቅና ከብርም ጋር አወጣቸው፥ በወገናቸውም ውስጥ የተደናቀፈ አልነበረም።


ወንዱ ከጎረቤቱ ሴቲቱም ከጎረቤቷ የብር ዕቃና የወርቅ ዕቃ እንዲጠይቁ በሕዝቡ ጆሮ ተናገር።”


ጻድቅ ሰው ለልጅ ልጆቹ ያወርሳል፥ የኃጢአተኛ ብልጥግና ግን ለጻድቅ ትጠበቃለች።


አንተ ሳትጠፋ የምታጠፋ፥ አንተም ሳትካድ ክህደትን የምትፈጽም ወዮልህ! ማጥፋትን በተውክ ጊዜ ትጠፋለህ፤ መካድን በተውክ ጊዜ ትካዳለህ።


በጦር መሣሪያው እሳትን ያነድዳሉ እንጂ እንጨትን ከሜዳ አይሸከሙም፥ ከዱርም አይቆርጡም፤ የዘረፉአቸውን ይዘርፋሉ የበዘበዙአቸውንም ይበዘብዛሉ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።