ዘፀአት 29:35 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለአሮንና ለልጆቹ እነዚህ ያዘዝሁህን ሁሉ አድርግ፤ ሰባት ቀን እጆቻቸውን ትቀድሳለህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ክህነታቸውን በሰባት ቀን በመፈጸም ለአሮንና ለወንዶች ልጆቹ ያዘዝሁህን ሁሉ አድርግላቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “አሮንና ልጆቹ የክህነት ሥልጣን የሚቀበሉበትን ሥርዓት ልክ እኔ ባዘዝኩህ መሠረት ለሰባት ቀን ፈጽም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “እንዳዘዝሁህም ሁሉ ለአሮንና ለልጆቹ እንዲህ አድርግ፤ ሰባት ቀን እጆቻቸውን ትቀድሳለህ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንዳዘዝሁህም ሁሉ በአሮንና በልጆቹ እንዲህ አድርግ፤ ሰባት ቀን ትክናቸዋለህ። |
ሰባት ቀን በየዕለቱ ለኃጢአት መሥዋዕት የሚሆነውን አውራ ፍየልን ታቀርባለህ፥ ነውር የሌለባቸውን ከመንጋው አንድ ወይፈን ከመንጋው አንድ አውራ በግ ያቀርባሉ።