ዘፀአት 29:30 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከልጆቹ በእርሱ ፈንታ ካህን የሚሆነው በመቅደስ ለማገልገል ወደ መገናኛው ድንኳን ሲገባ ሰባት ቀን ይልበሰው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ካህን በመሆን እርሱን የሚተካውና በመቅደሱ ለማገልገል ወደ መገናኛው ድንኳን የሚመጣው ወንድ ልጅ ሰባት ቀን ይለብሳቸዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የክህነቱ ሥልጣን ወራሽ በመሆን በተቀደሰው ስፍራ እኔን ለማገልገል ካህን ሆኖ ወደ ቅዱሱ ድንኳኔ የሚገባው የአሮን ልጅ እነዚህን ልብሶች ለሰባት ቀን ይልበስ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከልጆቹም በእርሱ ፋንታ ካህን የሚሆነው በመቅደስ ለማገልገል ወደ ምስክሩ ድንኳን ሲገባ ሰባት ቀን ይልበሰው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከልጆቹም በእርሱ ፈንታ ካህን የሚሆነው በመቅደስ ለማገልገል ወደ መገናኛው ድንኳን ሲገባ ሰባት ቀን ይልበሰው። |
ሰባት ቀን ያልቦካ ቂጣ ትበላላችሁ፤ በመጀመሪያው ቀን ከቤቶቻችሁ እርሾ ታስወግዳላችሁ፤ ከመጀመሪያውም ቀን አንሥቶ እስከ ሰባተኛው ቀን የቦካ የሚበላ ያቺ ነፍስ ከእስራኤል ተለይታ ትጥፋ።
ሙሴም አሮን የለበሰውን ልብስ አወለቀ፥ ልጁንም አልዓዛርን አለበሰው፤ አሮንም በዚያ በተራራው ራስ ላይ ሞተ፤ ሙሴና አልዓዛርም ከተራራው ወረዱ።