በመቅደሱ ለማገልገል ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊና ከቀይ ግምጃ በብልሃት የተሠራ ልብስ አደረጉ፥ ጌታም ሙሴን ባዘዘው መሠረት ለአሮን የተቀደሱ ልብሶችን ሠሩ።
ዘፀአት 28:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወርቅ፥ ሰማያዊ፥ ሐምራዊ፥ ቀይም ግምጃና ጥሩ በፍታም ይውሰዱ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወርቅ፣ ሰማያዊ፣ ሐምራዊ፣ ቀይ ማግና ቀጭን በፍታ ይጠቀሙ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጥበበኞቹም ልብሶቹን ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊ፥ ከቀይ ከፈይ ከወርቅ ምዝምዝና ከጥሩ በፍታ በጥልፍ አስጊጠው ይሥሩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወርቅ፥ ሰማያዊና ሐምራዊ፥ ቀይ ግምጃ፥ ጥሩ በፍታም ይውሰዱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወርቅንም፥ ሰማያዊና ሐምራዊ ቀይም ግምጃ፥ ጥሩ በፍታም ይውሰዱ። |
በመቅደሱ ለማገልገል ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊና ከቀይ ግምጃ በብልሃት የተሠራ ልብስ አደረጉ፥ ጌታም ሙሴን ባዘዘው መሠረት ለአሮን የተቀደሱ ልብሶችን ሠሩ።