ዘፀአት 28:25 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሁለቱን ድሪዎች ጫፎች በሁለቱ ፈርጦች ውስጥ አግብተህ በኤፉዱ ትከሻ በፊት ለፊት ታደርጋቸዋለህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሌሎቹን የጕንጕን ጫፎች በፊት ላይ ካለው ኤፉድ በትከሻው ላይ ካሉት ንጣዮች ጋራ በማጋጠም ከሁለቱ የወርቅ ፈርጦች ጋራ አያይዛቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በሌላ በኩል ያሉትንም የሁለቱን ድሪዎች ጫፎች ከሁለቱ ፈርጦች ጋር አገናኛቸው፤ በዚህም ዐይነት ከፊት ለፊት በኩል በትከሻ ላይ ከሚወርዱት ከኤፉዱ ማንገቻዎች ጋር ታያይዛቸዋለህ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሁለቱንም ቋዶች ጫፎች በሁለቱ ፈርጦች ውስጥ አግብተህ በልብሰ መትከፉ ጫንቃዎች ላይ በስተፊት በመጋጠሚያቸው ታደርጋቸዋለህ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሁለቱንም ድሪዎች ጫፎች በሁለቱ ፈርጦች ውስጥ አግብተህ በኤፉዱ ጫንቃዎች በፊታቸው ታደርጋቸዋለህ። |