ከሚጋጠሙት መጋረጆች በአንደኛው መጋረጃ ዘርፍ ላይ የሰማያዊውን ግምጃ ቀለበቶች አድርግ፤ ደግሞም ከተጋጠሙት ከሌሎች በአንደኛው መጋረጃ ዘርፍ ላይ እንዲሁ አድርግ።
ዘፀአት 26:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አምሳ ቀለበቶችን በአንድ መጋረጃ አድርግ፥ አምሳውንም ቀለበቶች በሁለተኛው መጋረጃ ዘርፍ አድርግ፤ ቀለበቶቹ ሁሉ እርስ በርሳቸው ፊት ለፊት እንዲሆኑ አድርግ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቀለበቶችን ትይዩ በማድረግ ዐምሳ ቀለበቶችን በአንደኛው ጠርዝ መጋረጃ፣ ዐምሳ ቀለበቶችንም በሌላው ጠርዝ መጋረጃ አድርግ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በመጀመሪያው መጋረጃ መጀመሪያ ክፍል ላይ ኀምሳ ቀለበቶች፥ በሁለተኛው መጋረጃ መጨረሻ ክፍል ላይ ከሌሎቹ ቀለበቶች ፊት ለፊት ኀምሳ ቀለበቶች አድርግ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አምሳ ቀለበቶችን በአንድ መጋረጃ አድርግ፤ አምሳውንም ቀለበቶች በሁለተኛው መጋረጃ ዘርፍ አድርግ፤ ቀለበቶቹ ሁሉ እርስ በርሳቸው ፊት ለፊት ይሆናሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አምሳ ቀለበቶችን በአንድ መጋረጃ አድርግ፥ አምሳውንም ቀለበቶች በሁለተኛው መጋረጃ ዘርፍ አድርግ፤ ቀለበቶቹ ሁሉ እርስ በርሳቸው ፊት ለፊት ይሆናሉ። |
ከሚጋጠሙት መጋረጆች በአንደኛው መጋረጃ ዘርፍ ላይ የሰማያዊውን ግምጃ ቀለበቶች አድርግ፤ ደግሞም ከተጋጠሙት ከሌሎች በአንደኛው መጋረጃ ዘርፍ ላይ እንዲሁ አድርግ።
አምሳ ቀለበቶችን በአንደኛው መጋረጃ አደረገ፥ አምሳ ቀለበቶች በሁለተኛው መጋረጃ ጠርዝ መጋጠሚያ አደረገ፤ ቀለበቶቹ እርስ በርሳቸው ፊት ለፊት የሚተያዩ ነበሩ።