ዘፀአት 26:27 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በማደሪያውም በሁለተኛው ወገን ላሉት ሳንቃዎች አምስት መወርወሪያዎች፥ በማደሪያውም በስተ ኋላ በምዕራብ ወገን ላሉት ሳንቃዎች አምስት መወርወሪያዎች አድርግ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሌላው ጐን ላሉት ዐምስት፣ በማደሪያው ድንኳን ዳር በምዕራብ በኩል ባሉት ወጋግራዎች ዐምስት አብጅ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አምስቱም በሌላው ጐን ላሉት ተራዳዎች የቀሩት አምስቱ ደግሞ በስተ ምዕራብ ከኋላ በኩል ላሉት ተራዳዎች ይሆናሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በድንኳኑ በሁለተኛ ወገን ላሉት ሳንቆች አምስት መወርወሪያዎችን፥ በድንኳኑም በስተኋላ በምዕራብ በኩል ላሉት ሳንቆች አምስት መወርወሪያዎችን አድርግ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በማደሪያውም በሁለተኛው ወገን ላሉት ሳንቆች አምስት መወርወሪያዎች፥ በማደሪያውም በስተ ኋላ በምዕራብ ወገን ላሉት ሳንቆች አምስት መወርወሪያዎች አድርግ። |