ዘፀአት 26:25 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስምንት ሳንቃዎችና ዐሥራ ስድስት የብር እግሮቻቸው ይሁኑ፥ ከእያንዳንዱም ሳንቃ በታች ሁለት እግሮች ይሆናሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ ስምንት ወጋግራዎች አሉ፤ እንዲሁም ዐሥራ ስድስት የብር መቆሚያዎች ሲኖሩ፣ ለእያንዳንዱ ወጋግራ ሁለት ሁለት መቆሚያ ይሆናል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚህ ዐይነት በእያንዳንዱ ተራዳ ሥር ሁለት እግር ሆኖ ዐሥራ ስድስት የብር እግሮች ያሉአቸው ስምንት ተራዳዎች ይኖራሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስምንት ሳንቆችና ዐሥራ ስድስት የብር እግሮቻቸው ይሁኑ፤ ከእያንዳንዱም ሳንቃ በታች በሁለቱም መጋጠሚያዎች ሁለት ሁለት እግሮች ይሆናሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስምንት ሳንቆችና አሥራ ስድስት የብር እግሮቻቸው ይሁኑ፤ ከእያንዳንዱም ሳንቃ በታች ሁለት እግሮች ይሆናሉ። |
መቶው የብር መክሊት የመቅደሱንና የመጋረጃውን እግሮች ለመሥራት ነበረ፤ ከመቶ መክሊት መቶ እግሮች ተሠሩ ይኸውም ለአንድ እግር አንድ መክሊት ማለት ነው።