አራት የወርቅ ቀለበቶችም አድርግለት፥ እነርሱንም በአራቱ እግሮቹ ላይ አኑር፤ በአንድ ወገን ሁለት ቀለበቶች፥ በሌላው ወገን ሁለት ቀለበቶች ይሁኑ።
ዘፀአት 25:26 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አራት የወርቅ ቀለበቶች አድርግለት፤ ቀለበቶቹንም አራቱ እግሮቹ ባሉበት በአራቱ ማዕዘኖች ላይ አድርጋቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለጠረጴዛው አራት የወርቅ ቀለበቶች ሠርተህ፣ አራቱ እግሮች ባሉበት በአራቱ ማእዘኖች ላይ አያይዘው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከወርቅ የተሠሩ አራት መሸከሚያ ቀለበቶች አድርግለት፤ ቀለበቶቹንም እግሮቹ ባሉበት በአራቱም ማእዘን አኑራቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አራትም የወርቅ ቀለበቶች አድርግለት፤ ቀለበቶቹንም አራት እግሮቹ ባሉበት በአራቱ ማዕዘኖች አድርግ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አራትም የወርቅ ቀለበቶች አድርግለት፤ ቀለበቶቹንም አራቱ እግሮቹ ባሉበት በአራቱ ማዕዘኖች አድርግ። |
አራት የወርቅ ቀለበቶችም አድርግለት፥ እነርሱንም በአራቱ እግሮቹ ላይ አኑር፤ በአንድ ወገን ሁለት ቀለበቶች፥ በሌላው ወገን ሁለት ቀለበቶች ይሁኑ።