ዘፀአት 25:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አንዱን ኪሩብ በአንድ በኩል፥ ሁለተኛውንም ኪሩብ በሌላው በኩል አኑር፥ በስርየት መክደኛው ላይ ኪሩቤል በሁለት በኩል ላይ ታደርጋቸዋለህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንዱን ኪሩብ በአንደኛው፣ ሁለተኛውን ኪሩብ በሌላኛው ዳር አድርግ በሁለቱም ጫፎች ሁለቱን ኪሩቤል ከስርየት መክደኛው ጋራ አንድ ወጥ አድርገህ ሥራቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በስርየት መክደኛውም ላይ በሁለት በኩል በጫፍና በጫፍ አኑራቸው፤ እነርሱም ከክዳኑ ጋር አብረው የተሠሩ ይሁኑ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከስርየት መክደኛውም ጋር አንዱን ኪሩብ በአንድ ወገን፥ ሁለተኛውንም ኪሩብ በሌላው ወገን አድርገህ በአንድ ላይ ትሠራዋለህ፤ ሁለቱንም ኪሩቤል እንዲሁ በሁለት ወገን ታደርጋቸዋለህ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከስርየት መክደኛውም ጋር አንዱን ኪሩብ በአንድ ወገን፥ ሁለተኛውንም ኪሩብ በሌላው ወገን አድርገህ በአንድ ላይ ትሠራዋለህ። |
ኪሩቤልም ክንፎቻቸውን ወደ ላይ ይዘረጋሉ፥ የስርየት መክደኛውንም በክንፎቻቸው ይሸፍናሉ፥ ፊታቸውም እርስ በርሱ ይተያያል፤ የኪሩቤልም ፊቶቻቸው ወደ ስርየት መክደኛው ይመለከታሉ።