ዘፀአት 23:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሚጠላህን ሰው አህያ ከሸክሙ በታች ወድቆ ብታየው አትተወው፥ ነገር ግን እንዲነሳ እርዳው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሚጠላህ ሰው አህያ፣ ጭነት ከብዶት ወድቆ ብታየው ርዳው እንጂ ትተኸው አትሂድ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሚጠላህ ሰው አህያ ከጭነቱ ክብደት የተነሣ ወድቆ ብታገኝ፥ አህያውን ከወደቀበት ለማንሣት እንዲችል እርዳው እንጂ አልፈኸው አትሂድ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የጠላትህን አህያ ከጭነቱ በታች ወድቆ ብታገኘው አትለፈው፤ ነገር ግን ከእርሱ ጋር ለማንሣት ርዳው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሚጠላህን ሰው አህያ ከሸክሙ በታች ወድቆ ብታየው አትተወው፥ ነገር ግን ከእርሱ ጋር አንሣው። |