La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘፀአት 22:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

መተተኛይቱን በሕይወት እንድትኖር አትፍቀድላት።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እርሷን ለርሱ የልጅቷ አባት በሚስትነት ለመስጠት ከቶ የማይፈቅድ ቢሆን፣ ለድንግሎች መከፈል የሚገባውን ማጫ አሁንም ቢሆን መክፈል ይገባዋል።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

የልጅትዋ አባት ሊድርለት ባይፈቅድ ግን ከአንድ ልጃገረድ ማጫ ጋር ተመጣጣኝ የሆነ የገንዘብ ካሣ ለልጅትዋ አባት ይክፈል።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

አባ​ቷም እር​ስ​ዋን እን​ዳ​ይ​ሰ​ጠው ፈጽሞ እንቢ ቢል እንደ ደና​ግል ማጫ ያህል ማጫ​ዋን ይስ​ጠው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

አባትዋም እርስዋን እንዳይሰጠው ፈጽሞ እንቢ ቢል እንደ ደናግል ማጫ ያህል ብር ይክፈላት።

Ver Capítulo



ዘፀአት 22:17
9 Referencias Cruzadas  

አብርሃምም ከኤፍሮን ጋር ተስማማ፥ በሒታውያንም ልጆች ፊት የነገረውን አራት መቶ ሰቅል በነጋዴዎች ሚዛን ልክ መዝኖ አብርሃም ለኤፍሮን ሰጠው፥ ብሩም ለመሸጫ ለመለወጫ የሚተላለፍ ነበረ።


ልያም፦ “እግዚአብሔር መልካም ስጦታን ሰጠኝ፥ እንግዲህስ ባሌ ከእኔ ጋር ይኖራል፥ ስድስት ልጆችን ወልጄለታለሁና” አለች፥ ስሙንም ዛብሎን ብላ ጠራችው።


ብዙ ጥሎሽና ስጦታ አምጣ በሉኝ፥ ይህችን ልጅ እንዳገባ ስጡኝ እንጂ፥ በነገራችሁኝም መጠን እሰጣለሁ።”


“የሙታን መናፍስት ጠሪዎችንና ጠንቋዮችንም በሚከተል፥ በሥራቸውም በሚያመነዝር፥ በዚያ ሰው ላይ ፊቴን አጠቊራለሁ፥ ከሕዝቡም መካከል ለይቼ አጠፋዋለሁ።


በመካከልህ ወንድ ወይም ሴት ልጁን በእሳት የሚሠዋ ሟርተኛ፥ ወይም መተተኛ፥ ሞራ ገለጭ፥ ጠንቋይ


ያ የደረሰባት ሰው አምሳ የብር ሰቅል ለብላቴናይቱ አባት ይስጥ፥ አስነውሮአታልና ሚስት ትሁነው፤ በዕድሜውም ዘመን ሁሉ ሊፈታት አይችልም።


ሳኦልም፥ “ዳዊትን፥ ‘ንጉሡም ለልጅቱ ካንተ የሚፈልገው ጥሎሽ ጠላቶቹን ለመበቀል የመቶ ፍልስጥኤማውያንን ሸለፈት እንጂ ሌላ አይደለም ብላችሁ ንገሩት’ ” አላቸው። ሳኦል ይህን ያቀደው ዳዊት በፍልስጥኤማውያን እጅ እንዲወድቅ ነበር።


በዚህ ጊዜ ሳሙኤል ሞቶ ነበር፤ እስራኤላውያንም ሁሉ በገዛ ከተማው በራማ አልቅሰው ቀበሩት። ሳኦልም ሙታን ሳቢዎችንና መናፍስት ጠሪዎችን ከምድሪቱ አባሯቸው ነበር።