ዘፀአት 21:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታዋን ደስ ባታሰኘው እንድትዋጅ ይስጣት፤ በድሎአታልና ለባዕድ ሕዝብ ሊሸጣት መብት የለውም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለርሱ ትሆነው ዘንድ የመረጣትን ጌታዋን ደስ ባታሠኝ፣ በወጆ ይስደዳት፤ ለባዕዳን ይሸጣት ዘንድ መብት የለውም፤ ምክንያቱም ለርሷ ያለውን ታማኝነት አጓድሏልና። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሚስት ሊያደርጋት ለፈለገ ሰው ብትሸጥና በኋላም እርሱ ሳይወዳት ቢቀር ተመልሳ በሕዝብዋ ትዋጅ ጌታዋ የማይገባ ነገር ስላደረገባት ለባዕድ ሊሸጣት አይችልም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለእርሱ ከታጨች በኋላ ጌታዋን ደስ ባታሰኘው በዎጆ ይስደዳት፤ ነገር ግን ለሌላ ወገን ይሸጣት ዘንድ አይገባውም። እርሱ አርክሶአታልና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጌታዋን ደስ ባታሰኘው በዎጆ ይስደዳት፤ ስለ ናቃት ለሌላ ወገን ሰዎች ይሸጣት ዘንድ አይገባውም። |
አባቱና እናቱም፥ “ከዘመዶችህ ወይም ከሕዝባችን ሁሉ መካከል ለአንተ የምትሆን ሴት መች ታጣችና ነው ወዳልተገረዙት አሕዛብ ዘንድ ሚስት ፍለጋ የሄድከው?” አሉት። ሳምሶንም አባቱን፥ “ልቤን የማረከችው እርሷ ናትና እርሷን አጋባኝ” አለው።
እንግዲህ ዛሬ በይሩበኣልና በቤተሰቡ ላይ ያደረጋችሁት በእውነትና በቅንነት ከሆነ እናንተ በአቤሜሌክ ደስ ይበላችሁ፤ እርሱም በእናንተ ደስ ይበለው
ሳኦል እጅግ ተቆጣ፤ ይህም ነገር አላስደሰተውም። እርሱም፥ “ለዳዊት ዐሥር ሺህ አሉለት፤ ለእኔ ግን ሺህ ብቻ! እንግዲህ መንግሥት እንጂ ሌላ ምን ቀረው!” አለ።