ዘፀአት 21:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ብቻውን መጥቶ እንደሆነ ብቻውን ይውጣ ከሚስቱ ጋር መጥቶ እንደሆነ ሚስቱ ከእርሱ ጋር ትውጣ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ብቻውን መጥቶ ከሆነ፣ ብቻውን በነጻ ይሂድ፤ ነገር ግን ሲመጣ ባለሚስት ከሆነ፣ እርሷ ዐብራው ትሂድ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ባሪያ እንዲሆንህ አንተ በገዛኸው ጊዜ ሚስት ያላገባ ከሆነ፥ ለቆ በሚወጣበት ጊዜ ብቻውን ይሂድ፤ ባሪያው በገዛኸው ጊዜ ሚስት አግብቶ ከሆነ ግን ሚስቱን ይዞ ይውጣ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ብቻውን መጥቶ እንደ ሆነ ብቻውን ይውጣ፤ ከሚስቱም ጋር መጥቶ እንደ ሆነ ሚስቱ ከእርሱ ጋር ትውጣ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ብቻውን መጥቶ እንደሆነ ብቻውን ይውጣ፤ ከሚስቱ ጋር መጥቶ እንደሆነ ሚስቱ ከእርሱ ጋር ትውጣ። |