ዘፀአት 21:29 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን በሬው አስቀድሞ ተዋጊ ቢሆን፥ ለባለቤቱ አስጠንቅቀውት ባይጠብቀውና ወንድን ወይም ሴትን ቢገድል፥ በሬው ይወገር፥ ባለቤቱ ደግሞ ይገደል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሆኖም በሬው የመውጋት ዐመል ያለበት ሆኖ ለባለቤቱም ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶት ሳለ በበረት ሳያስቀረው ቀርቶ አንድን ወንድ ወይም ሴት ቢገድል፣ በሬው በድንጋይ ይወገር፤ ባለቤቱም እንዲሁ ተወግሮ ይሙት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በሬው የተዋጊነት ልማድ ያለው ቢሆንና ባለቤቱም ቀደም ሲል ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶት በበረት ሳይዘው ቀርቶ ቢሆን ግን በሬው ሰው በሚወጋበት ጊዜ በድንጋይ ተወግሮ ይሙት፤ ባለ ንብረቱም በሞት ይቀጣ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሬው ግን ከትናንትና ከትናንት ወዲያ ተዋጊ ቢሆን፥ ሰዎችም ለባለቤቱ ቢመሰክሩለት ባያስወግደውም፥ ወንድን ወይም ሴትን ቢገድል፥ በሬው ይወገር፤ ባለቤቱ ደግሞ ይገደል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በሬው ግን አስቀድሞ ተዋጊ ቢሆን፥ ሰዎችም ለባለቤቱ ቢመሰክሩለት ባይጠብቀውም፥ ወንድንም ወይም ሴትን ቢገድል፥ በሬው ይወገር፥ ባለቤቱ ደግሞ ይገደል። |