ዘፀአት 21:21 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን የተመታው አንድ ወይም ሁለት ቀን ቢቆይ ገንዘቡ ነውና አይቀጣ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን ከአንድ ወይም ከሁለት ቀን በኋላ ባሪያው ቢነሣ መቀጣት የለበትም፤ ባሪያው ንብረቱ ነውና። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን ባሪያው በአንድ ቀን ወይም በሁለት ቀን ውስጥ ባይሞት አሳዳሪ ጌታው አይቀጣም፤ ባሪያውን ማጣቱ ራሱ ቅጣት ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የተመታው ግን አንድ ወይም ሁለት ቀን ቢቈይ ገንዘቡ ነውና አይቀጣ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የተመታው ግን አንድ ወይም ሁለት ቀን ቢቆይ ገንዘቡ ነውና አይቀጣ። |