ዘፀአት 2:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እረኞችም መጥተው ገፉአቸው፤ ሙሴ ግን ተነሥቶ ረዳቸው፥ በጎቻቸውንም አጠጣላቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እረኞችም መጥተው ሴቶቹን ሲያባርሯቸው ሙሴ ከተቀመጠበት ተነሥቶ ተከላከለላቸው፤ በጎቻቸውንም አጠጣላቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እረኞችም መጥተው እነዚያን ሴቶች አባረሩአቸው፤ ሙሴም ሴቶቹን ከእረኞቹ እጅ በማዳን መንጋቸውን ውሃ አጠጣላቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እረኞችም መጥተው ገፉአቸው፤ ሙሴ ግን ተነሥቶ አዳናቸው፤ እየቀዳም በጎቻቸዉን አጠጣላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እረኞችም መጥተው ገፉአቸው፤ ሙሴ ግን ተነሥቶ ረዳቸው፤ በጎቻቸውንም አጠጣላቸው። |
ያዕቆብም የእናቱን ወንድም የላባን ልጅ ራሔልንና የአጎቱን የላባን በጎች ባየ ጊዜ፥ ቀረበ ከጉድጓዱም አፍ ድንጋዩን ገለበጠ፥ የአጎቱን የላባን በጎችንም አጠጣ።
መንጎችም ሁሉ ከዚያ በተከማቹ ጊዜ ድንጋዩን ከጉድጓዱ አፍ ገለል አድርገው በጎቹን ያጠጡ ነበር፥ ድንጋዩንም ወደ ስፍራው መልሰው በጉድጓዱ አፍ እንደገና ይገጥሙት ነበር።