ዘፀአት 18:27 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሙሴም አማቱን ሸኘው፤ እርሱም ወደ አገሩ ተመለሰ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ሙሴ ዐማቱን በጕዞው ሸኘው፤ ዮቶርም ወደ አገሩ ተመለሰ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሙሴም ዐማቱን በሰላም አሰናብቶት፤ ወደ አገሩ ተመለሰ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሙሴም አማቱን አሰናበተው፤ እርሱም ወደ ሀገሩ ተመለሰ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሙሴም አማቱን ሰደደው፤ እርሱም ወደ አገሩ ተመለሰ። |
ሰውየውም ከቁባቱና ከአገልጋዩ ጋር ለመሄድ በተነሣ ጊዜ፥ የልጅቱ አባት ዐማቱ “እነሆ ጊዜው እየመሸ ነው፤ እዚሁ እደሩ፤ ቀኑ እየተገባደደ ነው፤ እዚሁ አድራችሁ ተደሰቱ፤ ነገ ጠዋት ማልዳችሁ በመነሣት መንገዳችሁን ትሄዳላችሁ” አለው።