አቤሴሎምም በማለዳ ተነሥቶ ወደ ከተማዪቱ መግቢያ በር በሚወስደው መንገድ ዳር ይቆም ነበር። ማናቸውም ባለ ጉዳይ አቤቱታውን ለንጉሡ አቅርቦ ለማስወሰን በሚመጣበት ጊዜ ሁሉ፥ አቤሴሎም ወደ እርሱ እየጠራ፥ “አንተ ከየትኛው ከተማ ነው የመጣኸው?” በማለት ይጠይቀዋል፤ ያም ሰው፥ “አገልጋይህ ከእስራኤል ነገዶች ከአንዱ ነው” ብሎ ይመልስለታል።
ዘፀአት 18:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሙሴ አማትም ለሕዝቡ ያደርግ የነበረውን ሁሉ ባየ ጊዜ፦ “ለሕዝቡ የምታደርገው ይሄ ነገር ምንድነው? ሕዝቡ ሁሉ ከጥዋት እስከ ማታ በዙሪያህ ቆመዋል፥ አንተ ብቻህን ለምን ተቀምጠሃል?” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዐማቱም ሙሴ ለሕዝቡ የሚያደርገውን ሁሉ ባየ ጊዜ፣ “ምን ማድረግህ ነው? እነዚህ ሁሉ ሰዎች ከጧት እስከ ማታ በዙሪያህ ቆመው ሳለ፣ ብቻህን በፍርድ ወንበር ላይ ለምን ትቀመጣለህ?” አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሙሴ ዐማት የትሮም ለሕዝቡ ያደርገው የነበረውን ሁሉ ከተመለከተ በኋላ እንዲህ ሲል ጠየቀው “ይህ ሁሉ ለሕዝቡ የምታደርገው ነገር ምንድን ነው? ሕዝቡ አንተን ለማነጋገር በመፈለግ ከጠዋት እስከ ማታ በዙሪያህ በመቆም እንደዚህ የሚያጨናንቅህና አንተም ይህን ሁሉ ጉዳይ በዳኝነት ለማየት ብቻህን የምትቀመጠው ለምንድነው?” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዮቶርም ሙሴ በሕዝቡ ላይ የሚያደርገውን ሁሉ አይቶ እንዲህ አለው፥ “ብቻህን ተቀምጠህ በሕዝቡ የምታደርገው ይህ ምንድን ነው? ሕዝቡ ሁሉ ከጥዋት ጀምሮ እስከ ማታ ድረስ በዙሪያህ ቆመዋል።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሙሴም አማት በሕዝቡ ያደረገውን ሁሉ ባየ ጊዜ፦ ይህ በሕዝቡ የምታደርገው ምንድር ነው? ሕዝቡ ሁሉ ከጥዋት ጀምሮ እስከ ማታ ድረስ በዙሪያህ ቆመው ሳሉ አንተ ብቻህን ስለ ምን ተቀምጠሃል? አለው። |
አቤሴሎምም በማለዳ ተነሥቶ ወደ ከተማዪቱ መግቢያ በር በሚወስደው መንገድ ዳር ይቆም ነበር። ማናቸውም ባለ ጉዳይ አቤቱታውን ለንጉሡ አቅርቦ ለማስወሰን በሚመጣበት ጊዜ ሁሉ፥ አቤሴሎም ወደ እርሱ እየጠራ፥ “አንተ ከየትኛው ከተማ ነው የመጣኸው?” በማለት ይጠይቀዋል፤ ያም ሰው፥ “አገልጋይህ ከእስራኤል ነገዶች ከአንዱ ነው” ብሎ ይመልስለታል።
የቄናዊው የሙሴ አማት ዘሮች ከይሁዳ ሰዎች ጋር በመሆን ከዘንባባዋ ከተማ ተነሥተው፥ ዓራድ አጠገብ በኔጌብ ውስጥ በይሁዳ ምድረ በዳ ካሉት ሕዝቦች ጋር አብረው ሄዱ፥ እዚያም ከሕዝቡ ጋር ተቀመጡ።