ዘፀአት 16:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሙሴም አሮንን፦ “ለእስራኤል ልጆች ማኅበር ሁሉ ‘ማጉረምረማችሁን ሰምቶአልና ወደ ጌታ ፊት ቅረቡ በላቸው’” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ሙሴ አሮንን፣ “ ‘ማጕረምረማችሁን እርሱ ሰምቷልና ወደ እግዚአብሔር ፊት ቅረቡ’ ብለህ ለመላው የእስራኤል ማኅበር ተናገር” አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሙሴ አሮንን፦ “እግዚአብሔር በእርሱ ላይ ማጒረምረማችሁን ስለ ሰማ፥ መላው የእስራኤል ማኅበር መጥታችሁ በእግዚአብሔር ፊት ቁሙ ብለህ ንገራቸው” አለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሙሴም አሮንን፥ “ለእስራኤል ልጆች ማኅበር ሁሉ፦ ‘ማንጐራጐራችሁን ሰምቶአልና ወደ እግዚአብሔር ፊት ቅረቡ’ በል” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሙሴም አሮንን፦ ለእስራኤል ልጆች ማኅበር ሁሉ፦ ማንጎራጎራችሁን ሰምቶአልና ወደ እግዚአብሔር ፊት ቅረቡ በል አለው። |
ሙሴም፦ “ጌታ በማታ የምትበሉትን ሥጋና በማለዳ ደግሞ የሚያጠግባችሁን ምግብ ሲሰጣችሁ ጌታ ያጉረመረማችሁበትን ማጉረምረም ሰምቶ ነው፤ እኛ ምንድን ነን? ማጉረምረማችሁ በጌታ ላይ ነው እንጂ በእኛ ላይ አይደለም” አለ።