ዘፀአት 16:32 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሙሴም፦ “ጌታ ያዘዘው ነገር ይህ ነው፦ ከግብጽ ምድር ባወጣኋችሁ ጊዜ በምድረ በዳ ያበላኋችሁን ምግብ እንዲያዩ ከእርሱ አንድ ዖሜር ሙሉ በትውልዳችሁ ሁሉ ይጠበቅ” አለ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሙሴም አለ፤ “እግዚአብሔር ያዘዘን ይህ ነው፤ ‘ከግብጽ ባወጣኋችሁ ጊዜ በምድረ በዳ እንድትበሉ የሰጠኋችሁን እንጀራ ያዩ ዘንድ አንድ ጎሞር መና ወስደህ ለሚመጡት ትውልዶች አቈየው።’ ” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሙሴም “እግዚአብሔር ያዘዘው ነገር ይህ ነው፤ ከግብጽ ምድር ባወጣኋችሁ ጊዜ በምድረ በዳ ያበላኋችሁን እንጀራ ያዩ ዘንድ ከእርሱ አንድ አንድ ኪሎ ተኩል ሙሉ ለልጅ ልጆቻችሁ ይጠበቅ።” አለ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሙሴም፥ “እግዚአብሔር ያዘዘው ነገር ይህ ነው፦ ከግብፅ ምድር በአወጣኋችሁ ጊዜ በምድረ በዳ ያበላኋችሁን እንጀራ ያዩ ዘንድ ከእርሱ አንድ ጎሞር ሙሉ ለልጅ ልጆቻችሁ ይጠበቅ” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሙሴም፦ እግዚአብሔር ያዘዘው ነገር ይህ ነው፦ ከግብፅ ምድር ባወጣኋችሁ ጊዜ በምድረ በዳ ያበላኋችሁን እንጀራ ያዩ ዘንድ ከእርሱ አንድ ጎሞር ሙሉ ለልጅ ልጆቻችሁ ይጠበቅ አለ። |
ነገር ግን፦ “ድምፄን ስሙ፥ እኔም አምላክ እሆናችኋለሁ እናንተም ሕዝብ ትሆኑኛላችሁ፤ መልካምም እንዲሆንላችሁ ባዘዝኋችሁ መንገድ ሁሉ ሂዱ” ብዬ በዚህ ነገር አዘዝኋቸው።
ሰብአዊ በሆነ የርኅራኄ ገመድ በፍቅርም እስራት ሳብኋቸው፤ ለእነርሱም ቀምበርን ከጫንቃቸው ላይ እንደሚያነሣ ሆንሁ፥ እነርሱንም ጐንበስ ብዬ መገብኳቸው።
በዚያም ውስጥ የወርቅ ማዕጠንት ነበር፤ ሁለንተናዋም በወርቅ የተለበጠች የኪዳን ታቦት፥ በእርስዋም ውስጥ መና ያለባት የወርቅ መሶብና የበቀለች የአሮን በትር የኪዳኑም ጽላት ነበሩ።