ዘፀአት 16:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዖሜርም በሰፈሩት ጊዜ ብዙ የሰበሰበው አልተረፈውም ጥቂት የሰበሰበውም አላነሰውም፤ የሰበሰቡት እያንዳንዱ የሚበላውን ያህል ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሰበሰቡትን በጎሞር በሰፈሩ ጊዜ፣ ብዙ የሰበሰበ አላተረፈም፤ ጥቂትም የሰበሰበ አልጐደለበትም፤ እያንዳንዱ የሰበሰበው የሚያስፈልገውን ያህል ሆነ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በሰፈሩትም ጊዜ ብዙ የሰበሰበው አልተረፈውም፤ ጥቂትም የሰበሰበ አላነሰበትም፤ እያንዳንዱ የሰበሰበው ልክ የሚበቃውን ያኽል ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በጎሞርም በሰፈሩት ጊዜ እጅግ ለሰበሰበ አልተረፈውም፤ ጥቂትም ለሰበሰበ አልጐደለበትም፤ ሁሉም እያንዳንዱ ሰው ለየቤቱ ሰበሰበ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በጎሞርም በሰፈሩት ጊዜ እጅግ ለለቀመ አልተረፈውም ጥቂትም ለለቀመ አልጎደለበትም፤ ሁሉ እያንዳንዱ የሚበላውን ያህል ለቀመ። |
ከእስራኤል ልጆች ርስት ለሌዋውያን የምትሰጡአቸውን ከተሞች እንዲሁ ስጡ፤ ከብዙዎቹ ብዙ፥ ከጥቂቶቹ ጥቂት ትወስዳላችሁ፤ እያንዳንዱ እንደ ወረሱት እንደ ርስታቸው መጠን ከከተሞቻቸው ለሌዋውያን ይሰጣሉ።”