ዘፀአት 16:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ ያዘዘው ነገር ይህ ነው፦ “እያንዳንዱ የሚበላውን ያህል ይሰብስብ፤ በድንኳኑ ባሉት ነፍሶች ቍጥር ለአንድ ሰው አንድ ዖሜር ይውሰድ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ያዘዘው ይህ ነው፤ ‘እያንዳንዱ የሚያስፈልገውን ያህል ይሰብስብ፤ በድንኳናችሁ ባለው ሰው ልክ ለእያንዳንዱ አንድ ጎሞር ውሰዱ’ ” ብሎ እግዚአብሔር አዝዟል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከእናንተ እያንዳንዱ የሚያስፈልገውን ያኽል ብቻ እንዲሰበስብ እግዚአብሔር አዞአል፤ ስለዚህ እያንዳንዱ የቤተሰብ አባል አንድ ኪሎ ተኩል ይውሰድ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ታደርጉት ዘንድ እግዚአብሔር ያዘዘው ነገር ይህ ነው፦ እያንዳንዱ ሰው ለቤተ ሰቡ ለእያንዳንዱ አንድ ጎሞር ይሰብስብ፤ እንደ ቤተ ሰቡ ቍጥር ለእያንዳንዱ በድንኳኑ አብረውት ከሚኖሩት ጋር ይሰብስብ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔር ያዘዘው ነገር ይህ ነው፦ እያንዳንዱ የሚበላውን ያህል ይልቀም በድኳኑ ባሉት ነፍሶች ቁጥር ለአንድ ሰው አንድ ጎሞር ውሰዱ አላቸው። |