ከግብጽም ከእነርሱ ጋር ያወጡትን ሊጥ ጋገሩ፥ አልቦካም ነበርና ቂጣ አደረጉት፤ ግብፃውያን በመውጣት ስላስቸኮሉአቸው ይቆዩ ዘንድ አልተቻላቸውም፥ ስንቅም አላሰናዱም ነበር።
ዘፀአት 12:34 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሕዝቡም ሊጡን ሳይቦካ ተሸከሙ፥ ማቡኪያውንም በልብሳቸው ጠቅልለው በትከሻቸው ተሸከሙት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ ሕዝቡ ያልቦካውን ሊጥ በየቡሖ ዕቃው አድርገው በጨርቅ ጠቅልለው በትከሻቸው ተሸከሙ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህም ሕዝቡ ያልቦካውን ሊጥ በቡሆ ዕቃ ሞልተው በልብስ በመጠቅለል በትከሻቸው ተሸከሙ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሕዝቡም ሊጡን ሳይቦካ ተሸከሙ፤ ቡሃቃውንም በልብሳቸው ጠቅልለው በትከሻቸው ተሸከሙት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሕዝቡም ሊጡን ሳይቦካ ተሸከሙ፤ ቡሃቃውንም በልብሳቸው ጠቅልለው በትከሻቸው ተሸከሙት። |
ከግብጽም ከእነርሱ ጋር ያወጡትን ሊጥ ጋገሩ፥ አልቦካም ነበርና ቂጣ አደረጉት፤ ግብፃውያን በመውጣት ስላስቸኮሉአቸው ይቆዩ ዘንድ አልተቻላቸውም፥ ስንቅም አላሰናዱም ነበር።
ሌላ ምሳሌ እንዲህ ሲል ነገራቸው፤ “መንግሥተ ሰማያት አንዲት ሴት ወስዳ ሁሉ እስኪቦካ ድረስ በሦስት መስፈሪያ ዱቄት ውስጥ የሸሸገችውን እርሾ ትመስላለች።”