ዘፀአት 12:31 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሙሴንና አሮንን በሌሊት ጠርቶ እንዲህ አላቸው፦ “እናንተ የእስራኤልም ልጆች ተነሡ፥ ከሕዝቤ መካከል ውጡ፤ ሂዱም፤ እንዳላችሁትም ጌታን አገልግሉ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ፈርዖን ሙሴንና አሮንን ሌሊቱን አስጠርቶ እንዲህ አላቸው፤ “ተነሡ፤ እናንተና እስራኤላውያን ከሕዝቤ መካከል ውጡ፤ ሂዱ፤ በጠየቃችሁት መሠረት እግዚአብሔርን አምልኩ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያኑ ሌሊት ንጉሡ ሙሴንና አሮንን አስጠርቶ እንዲህ አላቸው፦ “እናንተና እስራኤላውያን ወገኖቻችሁ ሁሉ ከዚህ ውጡ! አገሬን ለቃችሁ ሂዱ! በጠየቃችሁትም መሠረት ለእግዚአብሔር ስገዱ! የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፈርዖንም ሙሴንና አሮንን በሌሊት ጠርቶ አላቸው፥ “እናንተ የእስራኤልም ልጆች ተነሡ፤ ከሕዝቤ መካከል ውጡ፤ ሂዱም፤ እንዳላችሁም እግዚአብሔርን አምልኩት፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ፈርዖንም ሙሴንና አሮንን በሌሊት ጠርቶ፥ “እናንተ የእስራኤልም ልጆች ተነሡ፤ ከሕዝቤ መካከል ውጡ፤ ሂዱም፤ እንዳላችሁም እግዚአብሔርን አገልግሉ፤ |
ሙሴም፦ “ወጣቶቻችን፥ ሽማግሌዎቻችን፥ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችን፥ በጎቻችንና ከብቶቻችን ከእኛ ጋር ይሄዳሉ የጌታን በዓል እናደርጋለንና” አለ።
ጌታም ሙሴን እንዲህ አለው፦ “በፈርዖንና በግብጽ ላይ ገና አንድ መቅሰፍት አመጣለሁ፥ ከዚያ በኋላ ከዚህ ይለቅቃችኋል፤ ሲለቅቃችሁም ሙሉ በሙሉ ያባርራችኋል።
እነዚህም አገልጋዮችህ ሁሉ ወደ እኔ ይወርዳሉ፥ ለእኔም ይሰግዳሉ፥ ‘አንተ ውጣ በሥርህ ያለ ሕዝብ ሁሉ ይውጣ’ ይላሉ፤ ከዚያም በኋላ እወጣለሁ።” ሙሴም በጽኑ ቁጣ ከፈርዖን ዘንድ ወጣ።
ከግብጽም ከእነርሱ ጋር ያወጡትን ሊጥ ጋገሩ፥ አልቦካም ነበርና ቂጣ አደረጉት፤ ግብፃውያን በመውጣት ስላስቸኮሉአቸው ይቆዩ ዘንድ አልተቻላቸውም፥ ስንቅም አላሰናዱም ነበር።
ጌታም ሙሴን አለው፦ “አሁን ፈርዖንን ምን እንደማደርገው ታያለህ በጸናች እጅ ይለቅቃቸዋል፥ በጸናችም እጅ ከምድሩ አስወጥቶ ይሰድዳቸዋል።”
ሙሴም፦ “እነሆ እኔ ከአንተ ዘንድ እወጣለሁ፥ የዝንቡም መንጋ ከፈርዖን፥ ከአገልጋዮቹና ከሕዝቡ ነገ እንዲሄዱ ወደ ጌታ እጸልያለሁ፤ ነገር ግን ለጌታ ይሠዋ ዘንድ ሕዝቡን እንዳይለቅቅ ፈርዖን እንደገና አያታልለን” አለ።
ግብፃውያንና ፈርዖን እንዳደረጉት ልባችሁን የምታደነድኑት ለምንድን ነው? እነርሱ እስራኤላውያንን የለቀቋቸው እርሱ በጽኑ ከቀጣቸው በኋላ አይደለምን?