La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘፀአት 10:28 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ፈርዖንም፦ “ከእኔ ዘንድ ሂድ፤ ተጠንቀቅ፤ ፊቴን ባየህበት ቀን ትሞታለህና ፊቴን እንዳታይ” አለው።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ፈርዖን ሙሴን፣ “ከፊቴ ጥፋ! ሁለተኛ እኔ ዘንድ እንዳትደርስ! ፊቴን ባየህበት በዚያ ቀን ፈጽመህ እንደምትሞት ዕወቅ” አለው።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ስለዚህ ሙሴን “ዳግመኛ እንዳላይህ ከፊቴ ወዲያ ሂድ! እኔን በምታይበት ጊዜ እንደምትሞት ዕወቅ!” አለው።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ፈር​ዖ​ንም ሙሴን፥ “ከእኔ ዘንድ ሂድ፤ በፊቴ በም​ት​ታ​ይ​በት ቀን ትሞ​ታ​ለ​ህና ዳግ​መኛ ፊቴን እን​ዳ​ታይ ተጠ​ን​ቀቅ” አለው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ፈርዖንም፦ “ከእኔ ዘንድ ሂድ፤ ፊቴን ባየህበት ቀን ትሞታለህና ፊቴን እንዳታይ ተጠንቀቅ፤” አለው።

Ver Capítulo



ዘፀአት 10:28
6 Referencias Cruzadas  

አሳም በባለ ራእዩ ላይ ተቈጣ፤ ስለዚህም ነገር ተቈጥቶአልና በቊራኛ አስሮ በወህኒ ቤት አኖረው፤ በዚያን ጊዜም አሳ፥ ከሕዝቡ አያሌ ሰዎችን አሠቃየ።


እርሱም እየተናረ ሳለ ንጉሡ እንዲህ አለው፦ “በውኑ አንተ የንጉሡ አማካሪ ልትሆን ሾመነሃልን? ተው፤ እንዲገድሉህ ለምን ትሻለህ?” ነቢዩም፦ “ይህን አድርገሃልና፥ ምክሬንም አልሰማህምና ጌታ ሊያጠፋህ እንዳሰበ አወቅሁ” ብሎ ተወ።


እንዲህ አይሆንም፤ እናንተ ወንዶቹ ሂዱና ጌታን አገልግሉ፥ የጠየቃችሁት ይህንን ነውና።” ከፈርዖንም ፊት አባረሩአቸው።


የሁለተኛውም ስም ኤሊዔዘር ነበረ፦ “የአባቴ አምላክ ረዳኝ፥ ከፈርዖንም ሰይፍ አዳነኝ” ብሏልና።


ነገር ግን ቤቴል የንጉሥ መቅደስና የመንግሥት ቤት ናትና ከእንግዲህ ወዲህ በዚህ ዳግመኛ ትንቢት አትናገር።”


የማይታየውን እንደሚያየው አድርጎ ጸንቶአልና፥ የንጉሡን ቍጣ ሳይፈራ የግብጽን አገር ትቶ የሄደው በእምነት ነበር።