ኤፌሶን 6:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ባርያም ሆነ ነጻ ሰው፥ እያንዳንዱ ለሚያደርገው መልካም ነገር ሁሉ ከጌታ ብድራቱን እንደሚቀበል ታውቃላችሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምክንያቱም ባሪያም ሆነ ነጻ ሰው ለሚያደርገው በጎ ነገር ሁሉ ሽልማቱን ከጌታ እንደሚቀበል ታውቃላችሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ባሪያም ሆነ ጌታ እያንዳንዱ በሠራው መልካም ሥራ ከጌታ ዋጋውን የሚቀበል መሆኑን ታውቃላችሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጌታም ቢሆን፥ አገልጋይም ቢሆን መልካም ያደረገ ሁሉ በእግዚአብሔር ዘንድ ዋጋ እንደሚያገኝ ታውቃላችሁና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ባሪያ ቢሆን ወይም ጨዋ ሰው፥ እያንዳንዱ የሚያደርገውን መልካም ነገር ሁሉ ከጌታ በብድራት እንዲቀበለው ታውቃላችሁና። |
“ሰዎች እንዲያዩላችሁ ብላችሁ መልካምም ሥራችሁን በፊታቸው እንዳታደርጉ ተጠንቀቁ፤ አለበለዚያ በሰማያት ካለው አባታችሁ ዘንድ ሽልማት አታገኙም።
ነገር ግን ጠላቶቻችሁን ውደዱ፤ መልካምም አድርጉ፤ ይመለስልናልም ብላችሁ ምንም ተስፋ ሳታደርጉ አበድሩ፤ ዋጋችሁም ታላቅ ይሆናል፤ የልዑልም ልጆች ትሆናላችሁ፤ እርሱ ለማያመሰግኑና ለክፉዎች ቸር ነውና።
አይሁድ ብንሆን የግሪክ ሰዎችም ብንሆን ባርያዎችም ብንሆን ጨዋዎችም ብንሆን እኛ ሁላችን በአንድ መንፈስ አንድ አካል እንድንሆን ተጠምቀናልና። ሁላችንም አንዱን መንፈስ ጠጥተናል።
በዚህም መታደስ ግሪካዊና አይሁዳዊ፥ የተገረዘና ያልተገረዘ፥ አረማዊና እስኩቴስ፥ ባርያና ነጻ ሰው የሚባል ነገር አይኖርም፤ ነገር ግን ክርስቶስ ሁሉ ነው፤ በሁሉም ነው።