ኤፌሶን 5:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነርሱ በስውር ስለሚያደርጉት መናገር እንኳን ያስነውራል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በድብቅ የሚሠሩትን ነገር መናገር ራሱ አሳፋሪ ነውና። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በጨለማ የሚኖሩ ሰዎች በስውር ስለሚያደርጉት ነገር መናገር እንኳ ያሳፍራል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በስውር የሚሠሩት ሥራ ለመናገር የሚያሳፍር ነውና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነርሱ በስውር ስለሚያደርጉት መናገር እንኳ ነውር ነውና፤ |
አሕዛብ እንደሚያደርጉት በመዳራት፥ በሥጋዊ ምኞት፥ በስካር፥ በመሶልሶል፥ ያለ ልክ በመጠጣት፥ በአስነዋሪ የጣዖት አምልኮ የተመላለሳችሁበት ያለፈው ዘመን ይበቃል።
ሙታንን፥ እንዲሁም ታላላቆችንና ታናናሾችን በዙፋኑ ፊት ቆመው አየሁ፤ መጻሕፍትም ተከፈቱ፤ ሌላም መጽሐፍ ተከፈተ፤ እርሱም የሕይወት መጽሐፍ ነው፤ ሙታንም በመጻሕፍት በተጻፈው መሠረት፥ እንደ ሥራቸው መጠን ፍርድን ተቀበሉ።