ዔሳውም አባቱ ስለ ባረከው በያዕቆብ ቂም ያዘበት፥ ዔሳውም በልቡ አለ፦ “ለአባቴ የልቅሶ ቀን ቀርቦአል፥ ከዚያም በኋላ ወንድሜን ያዕቆብን እገድለዋለሁ።”
ኤፌሶን 4:31 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መራርነትና ንዴት ቁጣም፥ ጩኸትና ስድብን ሁሉ፥ ከክፋት ሁሉ ጋር ከእናንተ ዘንድ ይወገድ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም መራርነትን ሁሉ፣ ቍጣና ንዴትን፣ ጭቅጭቅና ስድብን ከማንኛውም ክፋት ጋራ ከእናንተ ዘንድ አስወግዱ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መራራነት፥ ንዴት፥ ቊጣ፥ ሁከት፥ ስድብና ማናቸውም ዐይነት ክፋት ሁሉ ከእናንተ ወዲያ ይራቅ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መራራነትንና ቍጣን፥ ብስጭትንና ርግማንን፥ ጥፋትንና ስድብን ሁሉ ከክፉ ነገር ሁሉ ጋር ከእናንተ አርቁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መራርነትና ንዴት ቁጣም ጩኸትም መሳደብም ሁሉ ከክፋት ሁሉ ጋር ከእናንተ ዘንድ ይወገድ። |
ዔሳውም አባቱ ስለ ባረከው በያዕቆብ ቂም ያዘበት፥ ዔሳውም በልቡ አለ፦ “ለአባቴ የልቅሶ ቀን ቀርቦአል፥ ከዚያም በኋላ ወንድሜን ያዕቆብን እገድለዋለሁ።”
እርሱም እንዲህ አለው፤ “ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፤ እኔ አገልጋይህ ሽባ በመሆኔ፥ ‘ከንጉሡ ጋር መሄድ እንድችል አህያዬ ይጫንልኝና ልቀመጥበት’ ብዬ ነበር፤ ይሁን እንጂ አገልጋዬ አታለለኝ።
የይሁዳም ሰዎች ሁሉ፥ ለእስራኤል ሰዎች፥ “ይህን ያደረግነው ንጉሡ የቅርብ ዘመዳችን ስለሆነ ነው፤ ታዲያ ይህ እናንተን የሚያስቆጣ ነገር ነው? እኛ ከንጉሡ ተቀብለን አንዳች በልተናልን? ለራሳችንስ ምን የወሰድነው ነገር አለ?” አሉአቸው።
ወደ እናንት ስመጣ፥ እኔ እንደምፈልገው ሆናችሁ ላላገኛችሁ እችላለሁ ወይም እናንተ እንደምትፈልጉኝ ሆኜ ላታገኙኝ ትችላላችሁ ብዬ እፈራለሁ፤ ምናልባት ክርክር፥ ቅንዓት፥ ቁጣ፥ አድመኝነት፥ ሐሜት፥ ማሾክሾክ፥ ኩራት፥ ሁከትም ይኖር ይሆን ብዬ እሰጋለሁ።
ከዚህም ጎን ለጎን ቤት ለቤት እየዞሩ ሥራ መፍታትን ይማራሉ፤ ሥራ ፈቶችም ብቻ ሳይሆኑ የማይገባቸውን እየተናገሩ ሰውን የሚያሙና በነገር ጣልቃ የሚገቡ ይሆናሉ።
ኤጲስ ቆጶስ እንደ እግዚአብሔር መጋቢ ነቀፋ የሌለበት ሊሆን ይገባዋል፤ የማይኮራ፥ የማይቆጣ፥ የማይሰክር፥ ጠበኛ ያልሆነ፥ ለገንዘብ የማይስገበገብ፥
እንዲሁም በዕድሜ የገፉ ሴቶች በመልካም ጠባያቸው የተቀደሱ፥ የማያሙ፥ ለብዙ ወይን ጠጅ ያልተገዙ፥ በጎ የሆነውን ነገር የሚያስተምሩ እንዲሆኑ ንገራቸው፤
ወንድሞች ሆይ! እርስ በርሳችሁ አትወነጃጀሉ፤ ወንድሙን የሚወነጅልና በወንድሙም ላይ የሚፈርድ በሕግ ላይ ክፉ ይናገራል፤ በሕግም ላይ ይፈርዳል። በሕግ ላይ ብትፈርድ ፈራጅ እንጂ ሕግን ፈጻሚ አይደለህም።
ከክፉው እንደነበረው ወንድሙንም እንደ ገደለው እንደ ቃየል አይደለም፤ ስለምንስ ገደለው? የእርሱ ሥራ ክፉ፥ የወንድሙ ግን ጽድቅ ስለ ነበረ ነው።
ታላቅም ድምፅ በሰማይ ሰማሁ፤ እንዲህ ሲል “አሁን የአምላካችን ማዳን፥ ኃይልም፥ መንግሥትም እንዲሁም የክርስቶስ ሥልጣን ሆነ፤ ቀንና ሌሊትም በአምላካችን ፊት የሚከሳቸው የወንድሞቻችን ከሳሽ ተጥሎአልና።