Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ራእይ 12:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 ታላቅም ድምፅ በሰማይ ሰማሁ፤ እንዲህ ሲል “አሁን የአምላካችን ማዳን፥ ኃይልም፥ መንግሥትም እንዲሁም የክርስቶስ ሥልጣን ሆነ፤ ቀንና ሌሊትም በአምላካችን ፊት የሚከሳቸው የወንድሞቻችን ከሳሽ ተጥሎአልና።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 ከዚህ በኋላ ታላቅ ድምፅ በሰማይ እንዲህ ሲል ሰማሁ፤ “አሁን የአምላካችን ማዳን፣ ኀይልና መንግሥት፣ የርሱ ክርስቶስ ሥልጣንም መጥቷል። ቀንና ሌሊት በአምላካችን ፊት ሲከስሳቸው የነበረው፣ የወንድሞቻችን ከሳሽ ተጥሏልና።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 ከዚህ በኋላ አንድ ታላቅ ድምፅ ከሰማይ እንዲህ ሲል ሰማሁ፤ “እነሆ አዳኝነት፥ ኀይል፥ መንግሥትም የአምላካችን ሆኖአል! ሥልጣንም የመሲሑ ሆኖአል! ወንድሞቻችንን በአምላካችን ፊት ቀንና ሌሊት ሲያሳጣቸው የነበረ የወንድሞቻችን ከሳሽ ተጥሎአል፤

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 ታላቅም ድምፅ በሰማይ ሰማሁ፤ እንዲህ ሲል “አሁን የአምላካችን ማዳንና ኀይል መንግሥትም የክርስቶስም ሥልጣን ሆነ፤ ቀንና ሌሊትም በአምላካችን ፊት የሚከሳቸውየወንድሞቻችን ከሳሽ ተጥሎአልና።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 ታላቅም ድምፅ በሰማይ ሰማሁ እንዲህ ሲል፦ አሁን የአምላካችን ማዳንና ኃይል መንግሥትም የክርስቶስም ሥልጣን ሆነ፥ ቀንና ሌሊትም በአምላካችን ፊት የሚከሳቸው የወንድሞቻችን ከሳሽ ተጥሎአልና።

Ver Capítulo Copiar




ራእይ 12:10
24 Referencias Cruzadas  

ጌታም “ስምዖን ስምዖን ሆይ! እነሆ፥ ሰይጣን እንደ ስንዴ ሊያበጥራችሁ ለመነ፤


ሰባተኛው መልአክ መለከቱን ነፋ፤ በሰማይም እንዲህ የሚሉ ታላላቅ ድምፆች ተሰሙ፦ “የዓለም መንግሥት የጌታችንና የመሢሑ ሆነች፤ ለዘለዓለምም እስከ ዘለዓለም ይነግሣል፤”


አቤቱ፥ በሰማይና በምድር ያለው ሁሉ የአንተ ነውና ታላቅነትና ኃይል፥ ክብርም፥ ድልና ግርማ ለአንተ ነው፤ አቤቱ፥ መንግሥት የአንተ ነው፥ አንተም በሁሉ ላይ ከፍ ከፍ ያልህ ራስ ነህ።


ኢየሱስም ቀረበና እንዲህ አላቸው “ሥልጣን ሁሉ በሰማይና በምድር ተሰጥቶኛል።


ነገር ግን እጅህን ዘርግተህ ያለውን ሁሉ ዳስስ፥ በእውነት በፊትህ ይሰድብሃል።”


ሰይጣንም ለጌታ እንዲህ ብሎ መለሰለት፦ “በውኑ ኢዮብ እግዚአብሔርን የሚፈራ በከንቱ ነውን?


ድል ለነሣውና እስከ መጨረሻም ሥራዬን ለጠበቀው እኔ ደግሞ ከአባቴ እንደ ተቀበልሁ በአሕዛብ ላይ ሥልጣንን እሰጠዋለሁ፤ በብረትም በትር ይገዛቸዋል፤ እንደ ሸክላ ዕቃም ይቀጠቀጣሉ፤


እርሱ ግን፥ “ጸጋዬ ይበቃሃል፤ ኀይሌ በድካም ፍጹም ይሆናል” አለኝ። እንግዲህ የክርስቶስ ኃይል እንዲያድርብኝ በበለጠ ደስታ በድካሜ መመካትን እወዳለሁ።


ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ “በማናቸውም ጊዜ ስትጸልዩ እንዲህ በሉ፦ ‘በሰማያት የምትኖር አባት ሆይ! ስምህ ይቀደስ፤ መንግሥትህ ትምጣ፤ ፈቃድህ በሰማይ እንደ ሆነች እንዲሁ በምድር ትሁን፤


ኢየሱስም “አንተ አልህ፤ ነገር ግን እላችኋለሁ፥ ከእንግዲህ ወዲህ የሰው ልጅ በኃይል ቀኝ ሲቀመጥና በሰማይ ደመና ሲመጣ ታዩታላችሁ” አለው።


መንግሥትህ ትምጣ፤ ፈቃድህ በሰማይ እንደሆነ እንዲሁም በምድር ይሁን፤


የምድር ዳርቻዎች ሁሉ ያስቡ፥ ወደ ጌታም ይመለሱ፥ የአሕዛብ ነገዶች ሁሉ በፊቱ ይሰግዳሉ።


ነገር ግን አሁን እጅህን ዘርግተህ አጥንቱንና ሥጋውን ዳስስ፥ በእውነት በፊትህ ይሰድብሃል።”


እንዲሁም በዕድሜ የገፉ ሴቶች በመልካም ጠባያቸው የተቀደሱ፥ የማያሙ፥ ለብዙ ወይን ጠጅ ያልተገዙ፥ በጎ የሆነውን ነገር የሚያስተምሩ እንዲሆኑ ንገራቸው፤


ከጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ኃይል ጋር፥ በጌታችን ኢየሱስ ስም ተሰብስባችሁ፥ መንፈሴም አብሮችሁ ነው፥


ኃያል ሆይ፥ ፍላጻዎችህ የተሳሉ ናቸው፥ እነርሱም በንጉሥ ጠላቶች ልብ ውስጥ ይገባሉ፥ አሕዛብም በበታችህ ይወድቃሉ።


በታላቅም ድምፅ እየጮሁ “ማዳን በዙፋኑ ላይ የተቀመጠው የአምላካችንና የበጉ ነው!” አሉ።


በመጠን ኑሩ፤ ንቁም! ጠላታችሁ ዲያብሎስ የሚውጠውን በመፈለግ እንደሚያገሣ አንበሳ ዙሪያውን ይንጐራደዳል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios